በመረጃው መሰረት በሽሬ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በስራ ማጣት ምክንያት ይሰቃዩ እንደነበሩና ያጋጠማቸውን የገንዘብ
ችግር ለመፍታት በኮብልስተን ስራ ተሰማርተው ሲሰሩ ቢቆዩም የጉልበታቸው ዋጋ ገንዘብ የሚከፍላቸው አካል ስለአጡ የተቃውሞ ሰላማዊ
ሰልፍ እንዳካሄዱ ለማወቅ ተችለዋል።
እነኚህ ወጣቶች የደከሙበትን የጉልበታቸው ዋጋ ገንዘብ እንዲከፈሉ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ ወደ
ዞን አስተዳደር በሄዱ ጊዜ በተቃውሞው የሰጉ የከተማዋ ባለስልጣናት። እንከፍላችኋለን በማለት የማታለያ ቃል እንደተናገሩና እስካሁን
እንዳልከፈሏቸው ለማወቅ ተችሏል።