Friday, June 13, 2014

ለሚቀጥለው 7 ዓመት በመከላከያ ለማገልገል አንፈርምም በማለታቸው የተሰናበቱ የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች የመኪና መሳፈሪያ አጥተው በየከተማው እየተንከራተቱ እንደሚገኙ ታውቋል።



    እኒህ አገልግሎታቸውን ጨርሰው ተጨማሪ 7 ዓመት እንዲፈርሙ ተጠይቀው አንቀበለውም በማለት ስንብት የጠየቁ የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች በቁጥራቸው በርካታ ሲሆኑ ከፍተኛ የሰራዊት  ሃላፊዎች ግን ጥያቄያቸውን መለስን ለማለት 1600 ለሚሆኑ ወታደሮች ብቻ ስንብት ሰጥተው ያለምንም ማቋቋሚያ  ገንዘብና የመኪና መሳፈሪያ ስለተሰናበቱ በሽሬ፤ ሸራሮ ጎዳናዎችና በሌሎችም በአካባቢው በሚገኙ ከተማዎች እየተንከራተቱ እንደሚገኙና ትልቅ ችግር የገጠማቸው መሆኑን ከሰራዊቱ መካከል የደረሰን መረጃ አመለከተ።
     አገልግሎታቸውን ጨርሰው የስንብት እድል ያላገኙ ወታደሮች በየቀኑ በቡድንና በግል ሰራዊቱን በመተው እግራቸው ወደ አመራቸው በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።