Tuesday, June 17, 2014

የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ተቃዋሚ ድርጅቶችን ከህዝብ ለመነጠል በተለያዩ አካባቢዎች እየፈነዱ የሚገኙ ፍንዳታዎች በተቃዋሚዎች እጅ የተፈፀሙ ናቸው እያለ በወንጀል እየፈረጃቸው መሆኑን ተገለፀ።



ሰኔ 4 2006 ዓ/ም በሽሬ ከተማ 05 ቀበሌ እንዳ ተኩሾ ተብሎ በሚጠራ መኖርያ ቤት መነሻው ባልታወቀው ምክንያት ቦምብ ፈንድቶ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነበሩ 3 ልጆች ሲሞቱ ሌላ አንድ ቆስሎ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።
ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ የስርአቱ ካድሬዎች የተቃዋሚ ድርጅቶች ሆን ብለው ህዝቡን ለማሸበር የፈፀሙት ተግባር ነው በማለት ቢያነሳሱም ያካባቢው ህዝብ ግን አሸባሪዎች የሉንም በማለት የካድሬዎቹን ቅስቀሳ ውድቅ ማድረጋቸው ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰኔ 6 2006 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ቃሊቲ አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ቆማ የነበረች ሰሌዳ ቁጥሯ 41-04-44 የሆነችው የፌደራል ፖሊስ ፓትሮል ተሽከርካሪ የጋየች ሲሆን በማን  እነደጋየችም እስካሁን እንዳልታወቀ መረጃው አክሎ አስረድቷል።