ታማኝ ምንጮች ከሁመራ ከተማ እንዳስታወቁት በከተማው ውስጥ ገንዘብ ተከፍሎ የሚገዛ የምግብ ዘይት ጠቅልሎ
በመጥፋቱ ምክንያት በማከፋፈያና ንግድ ድርጅቶች ሰልፍ ይዞ ብሬሽን መልክ ለአንድ ቤተሰብ ሩብ ሊትር ዘይት እየተሰጠው መሆኑን ለማወቅ
ተችለዋል።
ህዝቡ አጋጥሞት ባለው የምግብ ዘይት እጥረት
ተማሮ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እድገት አሳየን፤ ተለወጥን እያለ በሚናገርበት ባሁኑ ሰአት የምግብ ዘይትና ሌሎች አላቂ እቃዎች
ከከተማዋ ጠቅልለው መጥፋታቸው ስርአቱ በህዝቡ ላይ እየቀለደ መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲሉ ብሶታቸውን እየገለፁ መሆናቸው መረጃው አክሎ
አስረድተዋል።