Thursday, July 3, 2014

የላእላይ አድያቦ ወረዳ ወጣቶች በአካባቢያቸው ወደ ሚገኘው ወርቅ የሚለቅምበትን ቦታ ሰኔ 12/2006 ዓ/ም በተንቀሳቀሱበት ሰአት ለትህዴን ስንቅ ለማቀበል ስለፈለጋችሁ ነው ተብለው እንደታሰሩ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣፣



በላእላይ አድያቦ ወረዳ ጣብያ ዓዲ ክልተ ውስጥ የሚኖሩ በርካታ ሴትና ወንድ ወጣቶች ቃላይ ጨዖ ወደ ተባለ ልዩ ቦታ ሄደው ወርቅ ለመልቀም  በሞከሩበት ጊዜ በአካባቢው የሚገኙ የሰራዊትና የፖሊስ አባላት እናንተ ወርቅ ልትለቅሙ ሳይሆን ለትህዴን ስንቅ ልታቀብሉ እና ልትተባበሩ ነው በማለት ወርቅ ለቃሚዎችን እየቀጠቀጡ እንዳሰሯቸው ለማወቅ ተችሏል፣፣
   የቀበሌው ነዋሪ ህዝብ ደግሞ ከኣቅም በላይ ማዳበሪያ ውሰዱ ተብለን የወሰድነውን እዳ ምንከፍለው አጥተን እዳችንን ለመክፈል ላባችንን አፍስሰን ወርቅ በመልቀም እዳችንን እንዳንከፍል በገዛ ሃገራችን እንዳንኖር  በፖሊስና በወታደር ስማችን እየጠቆረና እየተደበደብን  እንታሰራለን በማለት በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ላይ  ምሬታቸውን እየግለፁ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፣፣