የትግራይ ህዝብ ያለፉትን የኣገራችን ጨቋኝ ገዢዎች ከስልጣናቸው ለመጣል
ለ17 ዓመታት ያህል ከሌሎች ብሄር ወንድሞቹ ጋር በመሆን ቃላት ሊገልፀው የማይችል መራራና ደማዊ ውጊያ ኣካሂዶ ከ65 ሺ በላይ
ልጆቹን መስዋእት ኣድርጎ ከ100 ሺ በላይ ወጣቶች ለኣካል ጉዳት ተዳርገው የደርግን ስርኣት ከስር መሰረቱ ኣሽቀንጥሮ በመጣል መራራ
የመስዋእት መድረክ ኣልፎ ድል የተጎናፀፈ ህዝብ ነው።
ሆኖም ግን ይህን የመሰለ የአኩሪ ታሪክ ባለቤትና የአገሩ አለኛታ የሆነ
የሚያድን ጀግና ህዝብ ታግሎና ደሙን ኣፍስሶ ባቖያት ሃገር እንደ
ዜጋ እፎይ ብሎ የሚኖርበት እድል ተስኖት እያለ የህወሓት መሪዎች የትግራይን ህዝብ እንደ መሰላል ተጠቅመው ወደ የስልጣን በመውጣት ዋናኞቹ የጥፋት ኣሽከርካሪዎች በመሆን ከዳር እስከ ዳር
ላለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ በአጠቃላይ ዴሞክራስያዊና ሰብኣዊ መብቱን በማፈን ኣበሳብሰውታል፣ በተጨማሪ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች
ብሄር ብሄረሰቦች በላይ የተለየ ጥቅም እንደሚያገኝና ትግራይ ክልል ወደ ላቀ የእድገት ደረጃ እንደተጓዘች የሚያስመስል የውሸት ፕሮፖጋንዳ
በመዘርጋት የትግራይ ህዝብ በሌሎች ብሄሔር ብሔረሰቦች ወንድሞቹ እንዲጠላና በመጥፎ ኣይን እንዲመለከቱት ያለ የሌለ ሃይላቸውን ተጠቅመው
ሰርቷል በመስራትም ላይ ይገኛሉ።
የትግራይ ህዝብ በገዛ አገሩ መሬት ጠቦት፤ኑሮው
ወደ ከፋ ደርጃ ወርዶ ከልክ ያለፈ ድህነት ከጫንቃው ላይ ተጭኖ እያሰቃየው ይገኛል፣ ይህንን ሁሉ ችግር ሊቋቋመው ያልቻለ ህዝብ
ደግሞ የደርግን ስርኣት ለመጣል ብሎ ስለ እሷ እየወደቁ በደማቸው የቀላች ኣገር እየተው እግራቸው ወደ ኣመራቸው ወደ ስደት እየጎረፉ
ናቸው፣ በዚ ምክንያት ደግሞ ብዙ የትግራይ ልጆች ልክ እንደሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ በሳህራ ምድረበዳዎች በረሃብና በውሃ ጥም
ወድቀው፤ የአረብ አገሮች “ዓሳችን እየጠገበ ነው” እያሉ መሳለቂያ እስከሚያደርጓቸው ድረስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ትግሬዎች ባህር
ሰምጠው የዓሳ እራት ሆኗል።
ይህ በንዲህ ሁኖ እያለም ህዝባችን በወያነ ስር ሁኖ ከመኖር የከፋ ነገር የለም በማለት ወደ ስደት መጉረፉ ኣላቋረጠም፣
በኣሁኑ ግዜ ኣገርህ ትተህ ወደ ስደት መውጣት እንደ ትልቅ እድል ነው የሚቆጠረው፣ ይህ ደግሞ ህዝባችን በወያነ ስርኣት ምክንያት
በኣገሩ ለመኖር ምን ያህል ተቸግሮ እንዳለ የሚያሳየን ትልቅ ምሳሌ ነው።
እነኝህ ህይወታቸውን ኣደጋ ላይ በተለያየ ግዝያት የስደት ጉዞ በለስ ቀንቷቸው በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ
ወገኖቻችን ህወሓት ኢህወዴግ የሚበላ ይኖራቸዋል ብሎ በመገመት ወደ ሰሜን ኤመሪካ ፤ አውሮፓ፤ኣወስትራልያና ማእከላዊ ምስራቅ አህጉሮች
የራሱ አጎብዳጅ የሆኑ ካድሬዎች በመላክ ሰፊና የማይተገበር የሚያስጎመጅ ፕሮፖጋንዳ በመለፈፍ ላባቸው ኣንጠፋጥፈው ሰርተው የሰበሰቡትን
ገንዘባቸው ለመቀማት ሲል በአገራቹህ ገብታቹ ኢንቨስት አድርጉ እያለ ዜጎቻችን “ዲያስፖራ” የሚል ስም ይዘው ወደ አገር ቤት እየገቡ
ናቸው።
እነዚህ ዲያስፖራ ወንድሞቻችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የሚጠላ ኢትዮጵያዊ
ዜጋ የለም፣ ሁኖም ግን በህወሓት ባለ ስልጣናት ተታልለው ገንዘባቸውን እንዳይከስሩ የብዙዎች ስጋት ሆኗል።
እነዚህ የተለየ
ቀና የዴሞክራሲና የአመራር አስተሳሰብ ያቀርቡ ለነበሩ የህዝብ ልጆች ትናንት ወያኔ ሲያሳድዳቸው እንዳልነበረ ዛሬ ደግሞ ገንዘብ
ይዘው የሚበላ ሲያገኝላቸው ወደ ኣገራችሁ ግቡና ኢንቨስት ኣድርጉ ሲል እየሰማነው ነው። መልካም አስተዳደር፤ የተረጋጋ የፖለቲካ
ሁኔት በሌለበት የተመቻቸ የንግድ ስራ በሌለበት አገር ኢንቨስት አድርጉ ማለት ገንዘባቸውን በአውላላ ሜዳ ላይ እንዲያፈሱት እየተገደዱ ይገኛሉ።
እነዚህ በወያኔ ስርዓት ምክንያት ኣገራቸውን ትተው የተሰደዱ ዜጎች ዛሬ ታዲያ
ምን ለውጥ ስላደረገ ነው ወደ ኣገራቸው ገብተው ገንዘባቸውን አፍስሰው ሃብት እንዲያካብቱ የሚለምናቸው? የዚህ ምክንያት ደግሞ እንደ
እስስት የሚገለባበጥ ባህሪ ያለው ስርኣት ንግግር እየቀየረ የተለመደው የማታለል ባህሪውን እየቀጠለበት ስላለ ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ ሃገራችን በአሁኑ ግዜ ዜጎችዋ ተሻማቀው የሚኖሩባት፤ ባእድ የሚኮራባትና
እንዳሻው ተንደላቅቆ የሚኖርባት ኣገር ሁና ነው ያለችው፣ የአገሪትዋ ዜጎች በኢንቨስትመንት ስም የእርሻ መሬታቸውን ያለ ምንም ካሳና
ተለዋጭ መሬት እየተነጠቁ። ከውጭ አገር ለመጡ የባእድ ኢንቨስተሮች ለአንድ ክፍለ ዘመን ያክል በእርካሽ ዋጋ የሚከራይባት የዜጎችዋ
ጉልበት በርካሽ የሚበዘበዝበት የእዩልኝ ስሙልኝ አገር ሁኗ ትገኛለች።
የትግራይ አቅም በፈቀደ ባለችው በደስታና በፈገግታ የሚያስተናግድ እንግዳ
ተቀባይ ህዝብ ነው፣ እነዚ ኣመራሮቹ ግን በሙስና የተጨማለቁና፤ ለሙስና እንደ ባህል የሚጠቀሙበት ስለሆኑ በዚ ዓመት በእንደርታ
ወረዳ ከምገኙ መንደሮች የአይናአለም፤ የዓዲ-ሓ እንዲሁም የእንዳማሪያም ህዝብ ከቀዩና ከመሬቱ በማፈናቀል ለትግራይ ዲያስፖራ ለቤት መስሪያና ለድርጅት እንዲሆን ተብሎ ከቦታው የተፈናቀለ
ህዝብ በመጥፎ የኑሮ ሁኔታ ባለበት ብትግራይ ዲያስፖራ ስም ዳንኬራ
መምታትና የእዩልኝ ስሙልኝ የሓሰት ጥሩባ በመቐለ ከተማ እየተነፋ ነው።
ይህ ተግባር አገር ውስጥም ሆኑ ውጪ ለሚኖሩ ብዝዋቹ የትግራይ ተወላጆች በኑሮአቸው ሆነ
ብእድገት ላይ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም፣ ምክንያቱም በስልጣን ላይ ያለ ገዥው መንግስት ይሁን በስልጣን ስስት በህዝብ ገንዘብ
እርስ በርሳቸው በመናቆር ላይ የሚገኙት የአዲስ አበባና የመቐለ ሁለት የህወሃት-ማሌሊት ስምምነት በሌላቸው በአጠቃላይ አገራችን
ኢትዮጵያ ብሙስና የጨቀዩ መሪዎችና ባለስልጣናት ባሉበት ፍትሕና መልካም አስተዳደር ስለማይኖር የተረጋጋ ጤናማ ስራና ኑሮ መምራት
ፈጽሞ የሚያመች አይደለም።
ይህ ችግር አሁን በዲያስፖራ
ስም ገብተው ባሉት የትግራይ ተወላጆች ልክ ከዚ ቀደም ከውጭ አገር ኢንቪስት እናረጋለን ብለው ገብተው ገንዘባቸውና ጉልበታቸው አፍስሰው
ስራ ከጀመሩ በኋላ ከአቅማቸው በላይ ግብር እንዲከፍሉ በመደረጋቸው ምክንያት ኪሳራ ውስጥ ስለወደቁ ድርጅታቸው ዘግተው ተመልሰ ወደ
ነበሩበት የስደት ኑሮ እንደተመለሱ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ጋህድ የሆነ ሓቅ ነው።
ትግራይ በዚ ሁኔት እያለች
ዲያስፖራዎች ጠርተሂእንቨስት አድርጉ መባሉ ለትግራይ እድገት ሳይሆን ከዲያስፖራው የሚገኝ የተለያየ ገቢ በመምዝበር ወደ የህወሓት-ማሌሊት
ካድሬዎች ካዝና ለማስገባት የታቀድ ነው።
በአሁኑ ግዜ በትግራይ ክልል በንግድ ስራዎች ሲሰሩ የቆዩ ዜጎቻችን ከአቅማቸው
በላይ የሆነ ግብር እንዲከፍሉ እያስገደዷቸው ኪሳራ ላይ ወድቀው ድርጅታቸውን ዘግተው ቁጭ ብለው እንዳሉ ለሁሉም የህብረተሰባችን
ክፍል ገሃድ የሆነ ሃቅ ነው። ትግራይ በዚ ሁኔታ እያለች ደግሞ ዲያስፖራዎችን እየጠራህ ኢንቨስት ኣድርጉ መባል የትግራይ እድገት
ሳይሆን የዲያስፖራዎች ካዝና በህወሓት ባለ ስልጣኖች ሲበዘበዝ እንታዘባለን።