Tuesday, August 5, 2014

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሶጌ ወረዳ ራስ ዳሽን የእርሻ ልማት በተባለው ቦታ የአቶ ሞላና የአቶ አለማየሁ የኢንቨስትመንት ድርጅት ዋና መጋዝን በመንግስት ታጣቂዎች ተመቶ መቃጠሉና የአንድ ሰው ህይወት ማለፉም ተገለፀ።



በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሶጌ ወረዳ በኢንቨስትመንት ለተሰማሩ አቶ ሞላና አቶ አለማየሁ የተባሉ ባለሃብቶች በተሰጣቸው ከ1800 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት ከመጠን በላይ የሆነ  ግብር እንዲከፍሉ የተጣለባቸው በመሆኑ ባለሃብቶችም እያለማነው ባለው 605 ሄክታር መሬት ልክ ግብር እንከፍላለን እንጂ ለ1800 ሄክታር አንከፍልም ማለታቸውን ተከትሎ በተነሳ አለመግባባት ሃምሌ 10 ቀን 2006 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ ከመንግስት ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ  የድርጅቱ መጋዝን እስከሙሉ ንብረቱ የወደመ መሆኑን የገለፀው መረጃው ከወደሙ ንብረቶችም በትንሹ ከ200 ኩንታል በላይ የአኩሪ አተር እና የማሽላ ምርት መቃጠሉና የድርጅቱ የፋይናንስ ሃላፊ አቶ ሚሊዮን የተባለ ተቀጣሪም ከታጣቂዎች በተተኮሰ 2 ጥይት ተመትቶ እንደተገደለ ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል።
   በተመሳሳይ! ጉግኖ እርሻ ልማት በተባለው የኢንቨስትመንት ፅ/ቤት ቢሮም በተጠቀሰው እለት እኒሁ የገዥው መንግስት ታጣቂዎች 4 ጥይት ተኩሰው ምንም ከቢሮው የወጣ ሰው ባለመኖሩ ተመልሰው ሊሄዱ እንደቻሉ ምንጮች አስረድተዋል።
  መረጃው ጨምሮም የድርጂቱ ስራ አስኪያጂ አቶ ከድር፤ የድርጅቱ ባለቤት አቶ አለማየሁና አቶ ሞላ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቢያቀርቡም ይህንን ጉዳይ ለ2ኛ ጊዜ እንዳያነሱ በማስጠንቀቂያ የተባረሩ መሆናቸውን አስረድቷል።