Wednesday, October 8, 2014

መደባይ ዛና ወረዳ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች መስከረም 22 /2007ዓ/ም የተሰበሰቡበት ዋናው ምክንያት በመጪው ግንቦት ወር ላይ በሚደረገው አስመስይ ምርጫ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆንን ተገለፀ።






በመረጃው መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ  ምዕራብ ዞን መደባይ ዛና ወረዳ ያሉት የእርሻ ሰራተኞች፤ መምህራን፤ ፖሊሶች፤ ሃኪሞችና የቀበሌዎች አስተዳደሮች የተገኙበት ስብሰባ። መስከረም 22 2007ዓ/ም በሰለኽላኻ ከተማ ውስጥ በወረዳዋ አስተዳዳሪ ተስፋይ ብርሃነ እንደተመራ የገለጸው መረጃው። የስብሰባው አጀንዳም መጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ላይ እያንዳንዱ የስብሰባው ተሳታፊ  ህወሓት-ኢህአደግን እንዲመረጥ ሃላፊነት መሰጠቱን ተረድቶ።  ግዴታውን መወጣት አለበት ሲል ባወረደው መምርያ በተሰብሳቢው ተቃውሞ እንዳጋጠመው ለማወቅ ተችሏል፣
    ተሰብሳቢዎቹ  ካነሱት ሃሳብም። መንግስት በቂ የዶሞዝ ጭማሪ እንዳደረገ አስመስሎ። በሚድያወቹ እያናፈሰው ያለው ወሬ ትክክል አይደለም ሲሉ ባቀረቡት አስተያየት የተናደደው የመድረኩ መሪው። ለተናገሩት ሰዎች በመድረኩ አስቁሞ ጸረ ልማታዊ መንግስታችንና ሃገራችን ናቸው ብሎ በመፈረጅ። መድረኩን ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ በማስፈራራትና ሰዎችን በመዝለፍ እንደጨረሰው  ለማወቅ ተችለዋል፣
    የተሰማቸውን ሃሳብ ስለገለጹ ብቻ በአስተዳደሩ ሂስ ከተደረጉ ዜጎች መካከል። መ/ር ንጉሰ ጎደፋይ ወለገርግስ፤ መ/ር ጎደፋይ ተስፋይ፤ ወ/ሮ ዙፋን  ሓድጉ የጤና ጣቢያ ሰራተኛና ሌሎችም ሲሆኑ። ለቀበሌ አስተዳዳሪዎችም በምርጫው እንድናሸንፍ ከተፈለገ። በቀበሌያችሁ የሚገኙ አደናቃፊዎች ቦታ አሳጧቸው የሚል ትእዛዝ እንዳስተላለፉላቸው። መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣