በመረጃው መሰረት- በማይካድራ
ከተማ የሚገኙ የገዥው በደብ ፖሊሶች መስከረም 17/2007 ዓ.ም የመስቀልን በዓል ለማክበር በወጣ ህዝብ ላይ በተኮሱት ጥይት ለጊዜው 3ት የታወቁ
ሰዎች በአሰቃቂ አገዳደል እንደተገደሉ ለማወቅ ትችሏል።
መረጃው አክሎ አነዚህ የከተማዋ ፖሊሶች በህዝቡ የተነሳውን ግጭት በዘዴ መፍታት
ሲገባቸው የመስቀልን በዓል ለማክበር በወጣ ህዝብ ላይ ህፃናት ሹማግሌዎች የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት ጥይት መተኮስ አግባብነት
የለውም በማለት የከተማዋ ነዋሪዎች ምሬታቸውን በመግለፀ ላይ እንዳሉ ምንጮቻችን አስታወቁ።
ፖሊሶቹ የፈጠሩት ችግር፤ ግርግርና አመፅ በተጥናከረ መልኩ ስለቀጠለ ይህንን
ለማረጋጋት ደግሞ የከተማዋ ፖሊሶች አቅም ስለሌላቸው ከሁመራ ከተማ የፌደራል ፖሊስና መደበኛ ፖሊስ በፓትሮል ተጭነው በመምጣት ለተፈጠረው
ግርግር ማረጋጋት እንደፈተኑ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አስታወቀ።