Tuesday, October 7, 2014

የትግራይ ምስራቃዊ ዞን አስተዳዳሪዎች በሙስና ስለተዘፈቁ የዞኑ ነዋሪ ህዝብ ከስልጣናቸው ይነሱልን በማለት ተቃውሞአቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻን አስታውቁ።



    በመረጃው መሰረት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የሚገኙ ከታችኛው እስከ ላየኛው የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙት አስተዳድሮች በሙስናና በስነ መግባር የተበላሹ እንዲሁም ህግ ወደ ጎን በመተው በዘመድ አዝማድ እየሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ በዚህ ምክንያት ደግሞ ነዋሪው ህብረተሰብ እነዚህ ሃገርን እያበላሹ ያሉ በሙስና የተዘፈቁ አስተዳዳሪዎች ከስልጣናቸው ይውረዱ በማለት ባገኙት አጋጣሚ ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ትችሏል።
  ስልጣናቸውን ተጠቅመው አድልኦ እየፈፀሙ ካሉ አስተዳዳሪዎች መካከል የጉሎ መኸዳ ተወላጆችና የብዘት መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ እነዚህ ሰዎች የስራ ሹመት ለመስጠት ይሁን ስራ ለመቅጠርና ሌሎችንም ጥቅማ ጥቅሞች ለአካባቢያቸው ተወላጆች፤ ለደጋፊያቸውና ለቤተሰቦቻቸው ቅድሚያ በመስጠት ስልጣናቸውን እየተጠቀሙበት በሆናቸውን የተረዳው ህብረተሰቡ እነዚህ አስተዳድሮች ይውረዱልን አያስተዳድሩንም በማለት ተቃውሞአቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አክሎ አስረድቷል።