Tuesday, October 7, 2014

አድዋ ከተማ ውስጥ ተሰብስበው የሰነበቱትን የመንግስት ሰራተኞች ያነሱትን ጥያቄዎች ለመድረኩ መሪዎች ጭንቀት እንደፈጠረላቸው የተገኘው መረጃ ገለጸ።



በትግራይ ማእከላዊ ዞን በዓድዋ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች በህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች ስብሰባ ላይ ተጠምደው መሰብሰባቸውን የገለፀው መረጃው የስብሰባው አጀንዳ የዴሞክራሲ ግንባታ ስርአትና የተሃድሶ መመር የሚል ቢሆንም ይህ ለማደናገር የቀረበው አጀንዳ ሊዋጥላቸው ያልቻለው ተሰብሳቢዎች ወቅታዊ ጥያቄዎች በማንሳት ካድሬዎቹን እንዳስጨነቛቸው ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።
ተሰብሳቢዎቹ ካስነሱት ጥያቄዎች በጥቂቱ ለመግለፅ- መሬትን በሊዝ መሸጥ ለባለሃብት እንጂ ለድሃው ህብረተሰብ ግምት የሰጠ አይደለም፤ ኪራይ ሰብሳቢነት አሰራር የኢህአዴግን አመራር መገለጫ በመሆኑ ፍትህና መልካም እስተዳደር ማስፈን አልተቻለም፤ መንግስት በሃይማኖት ላይ ጣልቃ እንደማይገባ በህገ መንግስቱ ላይ ቢያሰፍረውም በተለያየ መንገድ እየጣሰው ነው፤ መንግስት ነፃ ገበያ እንደሚፈቅድ መስሎ ቢናገርም ተመልሶ አዋጆችን በማፅደቅ ነጋዴዎች እንዳይሰሩ እንቅፋትና ጫና በመፍጠር ኪራይ ሰብሳቢነትን እንዲስፋፋ ምክንያት ይሆናል የሚሉና ሌሎች አስተያየቶች ባቀረቡበት ካድሬዎቹ ያላሰቡት ሁኔታ ስላጋጠማቸው ተደናግጠው በቂ ምላሽ ሳይሰጡበት መድረኩን እንደዘጉት መረጃው አክሎ አስረድተዋል።