Thursday, October 9, 2014







             የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፀረ ዴሞክራሲያዊ ተግባሮች
ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊባባስ እንጂ ልሻሻል ኣይችልም!!

    የኢህአዴግ ስርአት ከድሮም  ለህዝብ ጥቅም ያልቆመ የጥቂት ቡድን ጥርቅም መሆኑ ይታወቃል፣ ይህ ስርዓት ካለው ፀረ ህዝብ አካሄድ በመነሳት የራሱን ህዝብ ረግጦ በመያዝ እኔ ከሌለሁ ትበታተናለህ፤ የኢህአዴግ መስመር ዋነኛው የሃገርና የህዝብ ዋስትና ነው ወ.ዘ.ተ የሚል ኋላ ቀር አመለካከት አንግቦ። አገራችን ወደ አምባገነን አገዛዝ እንድትገባ ያደረገ የወቅቱ ፀረ ሰላም ስብስብ ነው፣


የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት ቀደም ብሎ እየሰራበት የቆየውን የአመፅ ተግባራት በሰፊው ለመጠቀም። በተለይ ከደርግ ስርአት ውድቀት ጀምሮ አገራችን ኢትዮጵያ በአንድ አምባገነን ስርአት እንድትመራ፤ የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚሳተፉበት መድረክ እንዳይፈጠር፤ ተወዳዳሪ በሌለበት የምርጫ ሂደት በአብላጫ ድምፅ እንዳሸነፈ አድርጎ በመግለፅና። በየወቅቱ የተካሄዱትን ምርጫዎች በስርቆትና በማጭበርበር የህዝቡን ድምፅ በማፈን አሸነፍኩ በማለት።  የአለምን ማህበረሰብ ሲያደናግር ቆይቷል፣
    የስርዓቱ ብልሹና ህገወጥ ድርጊት። ተፅፎና ተዘርዝሮ የሚያልቅ ባይሆንም። ዋነኞቹና መሰረታዊ የሆኑት። በተለይ የምርጫ ወቅት በሚቀራረብበት ጊዜ። የሚያካሂዳቸው የማደናገር ቅስቀሳና የሰብአዊ መብት ጥሰት። ካሁኑ ጀምሮ እያከናወናቸው ካሉት ጥቂቶቹን ለመግለፀ።-   
-   በሁሉም ያገራችን ክልሎች የሚገኝ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ። ለገዥው የኢህአዴግ ስርአት መምረጥ እንደሚገባው፤ ይህን ለማስፈፀም የሚያስችለው ስራ ለማካሄድም። ካሁን ጀምሮ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ተስፋ ለማጨለምና እንቅስቃሴዎቻቸውን ለመቆጣጠር እንዲቻል። በምርጫ ስም የሚካሄደውን ማንኛውም ተቃውሞ ጥብቅ ክትትል እንዲደረግለት መመርያዎችን መተላለፉ፤
-   እንደሚታወቀው ቀደም ሲል ህዝቡ በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ካሉት  ድርጅቶች ውስጥ አባል መሆን ካልቻለ እገዛ እንደማይደረግለት፤ የሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች አባል ሆኖ ከተገኘ። ቤት መከራየት፤ ከማህበረሰቡ ሊደረግለት የሚገባውን ማህበራዊ ትብብር በተለያየ መልኩ ጫና እንዲደረግበትና ከህብረተሰቡ ለመነጠል ሰፊ እንቅስቃሴ ይደረግ እንደነበረ ሁሉ። አሁንም ቢሆን ይህንን ፀረ ህዝብ ተግባር በማጠናከር። 2007 ዓ/ም በሚደረገው አስመሳይ ምርጫ ላይ ህጋዊና ሰላማዊ ባልሆነ መንገድ ለማካሄድ ታስቦ። ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የኢህአደግ መንግስት አባል ለመሆኑ የሚያረጋግጥ መለያ ካርድ እንዲይዝ የግዴታ ትእዛዝ ስለተሰጠው። ሳይወድና ከስራ ገበታው እንዳይባረር በመስጋት መመርያውን ተግባር ላይ ማዋል ግድ ሆኖበታል፣ ይህ የስርአቱ ብልሹና ርካሽ ተግባርም። በይፋ እየተፈፀመ ያለውን ፀረ ዴሞክራሲያዊና አይን ያወጣ የመብት ጥሰት። ሲበዛ ግልፅ ያደርገዋል፣  
    ለማጠቃለል።- የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት ነጋ ጠባ ጉራ የሚነዛለትና። ለእዩልኝ ስሙልኝ ብቻ በሚናገርለት የምርጫ ሂደት። ገና ሳይካሄድ አሸናፊ እንደሚሆን ቢያውቅም። ለማስመሰል ብሎ ግን።የአለም ማህበረሰብ ለመደናገር። ባንድ በኩል የ2007 ዓ/ም ምርጫ። ህጋዊ፤ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሊሆን እንደሚችል ተናግሮ ሲያበቃ። በሌላ በኩል ደግሞ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛና ሌላው ማህበረሰብ። ኢህአዴግን መምረጥ እንደሚገባው የሚያስገድድ የማስፈራሪያ ትእዛዝ ማውረዱ። ፈፅሞ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መሆን እንደማይችል ግልፅ ምልክት እየሰጠን ነው፣
   የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ይህ በኢህአዴግ እየተመራ በየግዜው የሚካሄደውን አስመሳይ ምርጫ። ለፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ የሚጎስም ነጋሪት መሆኑን አውቀህ። ሃቀኛ የህዝብ መንግስት ለትከል አሁንም እንዳለፈው በጠላቶችህ ላይ ክንድህን ማሳረፍ እንደሚገባህ መዘንጋት የለብህም፣ ምክንያቱም የኢህአዴግ ፀረ ዴሞክራሲያዊ ተግባር ከግዜ ወደ ግዜ ሊባባስ እንጂ ልሻሻል  ኣችልም!!