Tuesday, December 23, 2014

በአፋርና ሶማሌ ክልል መካከል ሲያነታርክ የቆየውን የ3 ከተማዎች የይገባኛል ጥያቄ ወደ አፋር ክልል እንዲሆኑ በስርአቱ ውሳኔ ስለተሰጠበት በሁለቱ ህዝቦች ከባድ ግጭት መነሳቱ ተገለፀ።



    በአፋርና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ የነበረው መሬት በየትኛው ክልል እንደነበር በግልፅ የተቀመጠ መረጃ ባለመኖሩ የተነሳ እስከ ህይወት መገዳደል የሚያደርስ ግጭት እያጋጠመ መቆየቱን የገለፀው መረጃው ስርአቱ በዝምታ እያየ ቆይቶ በቅርብ ግዜ ችግሩን መፍትሄ አድርጌበታለሁ በሚል ሦስቱም ከተማዎች ወደ አፋር ክልል እንዲጠቃለሉ በማድረጉ በሶማሌ ክልል ህዝብ ተቀባይነት እንዳላገኘና በሁለቱም ክልል ህዝብ ከባድ የደም ማፋሰስ ግጭት ማስነሳቱን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
     ታህሳስ 5 / 2007 ዓ/ም በሁለቱም ክልል ህዝቦች መካከል ለአንድ ቀን ያህል ሲካሄድ በዋለው በመሳርያ የተደገፈ የተኩስ  ግጭት በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡና የቆሰሉ ሲሆኑ ይህ አሰቃቂ የደም ማፋሰስ ግጭትም የስርአቱ ጭፍን ውሳኔ ውጤት መሆኑንና ተጠያቂውም የኢህአዴግ ስርአት እንደሆነ ህዝቡ መግለፁን መረጃው አክሎ አስረድቷል።