Tuesday, December 23, 2014

በትግራይ ውስጥ የሚገኙ የሰማእታት ቤተሰቦች በስራ አጥነት በመቸገራቸው ምክንያት ስርአቱ መፍትሄ እንዲያደርግላቸው በማለት ብሶታቸውን እንዳቀረቡ የተገኘው መረጃ ገለፀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ውስጥ የሚገኙ የሰማእታት ቤተሰቦች ትምህርታቸውን ጨርሰው የስራ እድል ማግኘት ስላልቻሉ ችግራችንን የሚፈታልን ወገን አጣን፤ ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ትኩረት ያድርግልን፤ ትግራይ ውስጥ ባሉ የትእምት ድርጅቶች ተቀጥረን እንድንሰራ እድሉ ይሰጠን ሲሉ ወደ ትግራይ ክልል ባለ ስልጣኖች ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለፀ።
   መረጃው ጨምሮ እነኝህ በትግራይ ህዝብ ገንዘብ የቆሙት የትእምት ድርጅቶች ሰራተኞች ሲቀጥሩ ባላቸው ትምህርትና ሞያ መዝነው ሳይሆን በቤተሰብና በጉቦ ስለሆነ እኛ ደግሞ ለጉቦ የሚሆን ገንዘብ ስለሌለን ትኩረት ይደረግልን? የአባቶቻችን ደም የፈሰሰባቸው ድርጅቶች አይደሉምን? በማለት በተደጋጋሚ ጠይቀው ሰሚ ጀሮ እንዳላገኙና አብዛኛው የትግራይ ህዝብም ድርጅቶቹ ለስርአቱ ባለስልጣናት ብቻ እያገለግሉ ናቸው በሚል በከፍተኛ ቅሬታ ላይ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል።