Sunday, December 14, 2014

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ተቃዋሚ ድርጅቶች ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርጉ ስለተከለክከሉ ህዝብ የሚያነሳሱ ፓምፕሌቶች በብዛት በመበተን ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



    በኦሮሚያ ክልል ነቀምትና ሻንቦ ከተማዎች ውስጥ የሚገኘው ህዝብ በኦሆዴድ ኢህአዴግ ስርአት ላይ ያለው ጥላቻ ከፍተኛ መሆኑን የገለፀው መረጃው ያለውን ጥላቻ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሰላማዊ ሰልፍ ይሁን ስብሰባ እንዳያካሄድ ስለአገዱት በአንጻሩ ስርአቱን በመቃወም የተለያዩ ቅስቀሳዎችን እያካሄዱ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
   መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው በከተማዎቹ የሚኖረው ህዝብ በማህበራዊ አቅርቦት ችግርና መልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት ለከባድ ችግር ስለተጋለጠ ለችግሩ መፍትሄ ይሆናል ብለው በተቃዋሚዎች የሚሰራጩ ፓምፕሌቶችን ይዘታቸውን አይቶ በመረዳት አይዟችሁ ከጎናችሁ አለን በስልጣን ላይ ላለው የኢህአዴግ መንግስት ድምፃችን አንሰጥም በማለት ለተቃዋሚ ድርጅቶች የሞራል ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።