Sunday, December 14, 2014

በአክሱም ከተማ የህዳር ፅዮንን በዓል ለማክበር የተሰበሰቡ መዕመናን የገዥው ስርዓት የድህነት አባላት አሽባሪዎች ገብተዋል በማለት ባሰራጩት ወሬ ተደናግጠው ከቤተክርስትያኑ ሸሽተው እንደወጡ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።



በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አክሱም ከተማ የሚገኙ የስርዓቱ የደህንነት አባላት ህዳር 21/2007 ዓ,ም አሸባሪዎች ወደ ከተማችን ገብተዋል በማለት ባሰራጩት የሃሰት ወሬ በዓሉን ለማክበር የመጡ እንግዶችና ነዋሪዎች በከባድ ስጋት ላይ እንደወደቁ የገለፀው ይህ መረጃ በተለይ ደግሞ ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች የህዳር ፅዮንን በዓል ለማክበር የተሰበሰቡ አማኞች በተሰራጨው የሃሰት ወሬ ተደናግጠው በሚሊዮኖች የሚገመት ንብረት ትተው እንደሸሹ ሊታወቅ ተችሏል።
   መረጃው አክሎ የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች በስርዓቱ የደህንነት አባላት የተሰራጨው ወሬ የሃሰት ወሬ መሆኑን ከገለፁ በኋላ ምንም ነገር በከተማችን የተፈጠረ ነገር ሳይኖር በዓሉን ለማክበር የመጡ ምዕመናን በዓሉን ትተው እንዲሸሹና ወደ ፀሎታቸው እንዳይመለሱ እንዲደናገጡ አድርጋችኋል በማለት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ እየገለፁ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
     ይህ በእንዲህ እንዳለ ፀረ ህዝብ የሆኑ የስርዓቱ አገልጋይ  ጋዜጠኞች በቴሌቭዥን መስኮት አንዳንድ ሰዎችን እንዲናገሩ በማድረግ በዓሉ ያለምንም እንቅፋት እንደተከበረ ለማስመሰል  ያደረጉት ቃለ መጠየቅ በዞኑ የድህነት አባላት የተፈጠረውን እኩይ ተግባራቸውን ለመሸፈን የተደረገ መሆኑንና የአካባቢው ህዝብ መነጋገርያ አጀንዳቸው አድርገውት እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አመልክቷል።