Wednesday, December 17, 2014

በትግራይ ክልል ዋና ዋና መስመሮች ላይ በርካታ የፍተሻ ኬላዎች ስለተቋቋሙ ነዋሪው ህዝብ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ዕለታዊ ስራውን ማሳለጥ እንዳልቻለ ተገለፀ፣፣



ምንጮቻችን እንደገለፁት በውስጣዊ ችግሮቹ ሊረጋጋ ያልቻለው ገዥው  የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ቡድን በተበላሸ አስተዳደሩ የተጎዳውን የትግራይን ህዝብ በነፍስ ወከፍ በጥርጣሬ አይን እያየ እየተከታተለውና እየጠበቀው እንዳለ የገለፀው መረጃው ይህንንም ለመተግበር በሽረ፥ ሽራሮ፥ በአክሱምና ሁመራ አቋርጦ በሚያልፈው መንገድ ላይ ኬላዎችን በማቋቋም ዘግቶ እንደሚገኝና በስፍራው የተሰማሩ ፖሊሶችና ወታደሮችም በእግር ይሁን በመኪና የሚንቀሳቀሰውን ሰው ወዴት ነህ? ከየት መጣህ? የመታወቂያ ወረቀት አምጣ እያሉ እያንገላቱት እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፣፣
   መረጃው ጨምሮም እየተካየደ ባለው ስርዓት አልባ ፍተሻ በረካታውን ህዝብ የመታወቂያ ወረቀት አልያዝክም አልታደሰም በማለት እያሰሩ እያሰቃዩት እንደሚውሉ ከገለፀ በኋላ እኛን ምን አድርጉ ትሉናላችሁ የመታወቂያ ወረቀት ማውጣትና ማሳደስ ወደ አስተዳደር በተደጋጋሚ ተመላልሰን ነገ ዛሬ እየተባልን ቀጠሮ ስለበዛብንና ፍትህ ማገኘት ስላልቻልን ተንቀሳቅሰን ኑሮአችንን ለመምራት ስንል ያደረግነው ነው በማለት በምሬት እየተናገሩ እንደሆኑ አስረድተዋል።