Wednesday, February 18, 2015

የካቲት 11/2007 ዓ/ምን በማስመልከት ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ / ትህዴን / የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ!!



የካቲት 11/2007 ዓ/ምን በማስመልከት ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ / ትህዴን / የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ!!

    የትግራይ ህዝብ ለረጅም አመታት ባካሄደው መራራ ትግል ከባድና የመይቻል ተደርጎ ይታይ የነበረውን የትጥቅ ትግል እውን ያደረገ ከፍተኛ የጀግንነት ገድል የሰራና ከባድ ዋጋ ከፍሎ መጨረሻ ላይ ወደ ድል የደረሰ ልዩ ታሪካዊ ህዝብ ነው።
    ህዝቡ  ለጭቆና፤ ለሰቆቃና በላዩ ላይ ይደርስ የነበረውን ፀረ ህዝብ አገዛዝ በመቃወም እምቢ አልምበረከክም በማለት መስዋእት በመክፈል የግድ ድልን እጎናፀፋለሁ ብሎ ትግሉን ሲጀምር የባሰውን አፋኝ ስርዓት ለማምጣት ሳይሆን ህዝባዊ ስርአትን ለመተካት በማሰብ ነበር።
   ቢሆንም ግን በጥባጭ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣል እንደሚባለው የህወሃት መሪዎች ያን ያህል የተከፈለውን መስዋእትነት ከንቱ እንዲቀር በማድረግ በሺዎች የተከፈለለትን መስዋእትነትና መጠነ ሰፊ የአካል ጉዳት የተፈፀመበት አኩሪ ታሪክ ለግል ጥቅማቸውና ለአጃቢዎቻቸው ጥቅም እንዲውል በማድረግ የመላው ህዝባችን ተስፋ እንዲጨልም አድርገውታል።
     የትግራይ ህዝብ የካቲት 11ን በትጥቅ ትግል ወቅት ሲያከብረው የዛሬውን እያድርገውና በድርጅቱ ተገዶ ሳይሆን በራሱ ፍላጎትና ተነሳሽነት ለእለቱ ከፍተኛ ክብር በመስጠትና የችግሩን ዋና መፍትሄ አድርጎ በመቁጠር በየአመቱ ተስፋዎችን በመሰነቅ እያከበረው እንደነበር ታሪክ ይነግረናል።
     ዛሬ ግን እንደድሮው ከፍተኛ ክብር ሰጥቶ ማክበር ይቅርና ስሟን ለማሳት እንኳ አስጠልቶት እና ለስሟና ለክብሯ ብለን መስዋእት ከፈልን እንጂ የተጠቀምነው ነገር የለም እያለና የባሱ ጨቋኞችን አመጣን እያለ ሲያማርርና ብሶቱን ሲገልፅ ይስተዋላል።
   ይህ ለ40 ግዜ የልደት በዓልን ለማክበር ተብሎ በህወሃት አመራሮች ከመጠን በላይ የህዝብና የሃገርና ሃብት ወጪ ተደርጎበት እየተዘጋጀ ያለውን በዓል ለህወሃት ፀረ ህዝብ አመራሮችና ተከታዮቻቸው እንጂ ለጭቁኑ ህዝብ የሚወክል አይደለም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ በላዩ ላይ ይደርስ ከነበረው ግፍ ለመላቀቅ ብሎ በታገለለት መስመር ጥቅሙ ሊረጋገጥለት ስላልቻለ።  
   የተከበርህ የትግራይ ህዝብ ሆይ የህወሃት አመራሮች ራስህ በከፈልከው ወደር የለሽ መስዋእትነት ወደ ስልጣን ወጥተው በረሃብ እየተሰቃየህ ባለህበት ባሁኑ ጊዜ ጥቅም እንዳገኘህና እድገት እንዳስመዘገብህ፤ እነሱ ማለት እንተ እንደሆንህ አስመስለው በሚያቀርቡት የሃሰት ድራማ አገራችን ባሉት ብሄር ብሄረሰቦች ጥላቻ ውስጥ እንድትገባና በጥርጣሬ አይን እንድትታይ እያደረጉ መጥተዋል።
    ይህ ሁኔታ ግን ፍፁም ሃሰት እነደሆነና እውነታው የተገላቢጦሽ መሆኑን ማለት እነዚህ ከህዝቡ ፍላጎትና ተሳትፎ ውጭ ስልጣን ላይ የሚገኙት ጥቂት የስርዓቱ ጸረ ህዝብ አመራሮች አንተን እንደማይወክሉና ይባሱን ከማንኛውም በላይ በመሪዎቹ ክህደት የተፈፀመብህ መሆንህን በሚገባ ታውቀዋለህ። የህወሃት ሽማሙንት አመራሮች በህዝቡ ላይ የሚያካሂዱትን የማደናገር ተግባር በመቀጠል አሁንም በበዓሉ ምክንያት እያመካኙ ቀጣይ ስልጣን ላይ ለመቆየት ካላቸው ፍላጎት በመነሳት በተለያየ መንገድ የአዞ እንባ እያነቡ የልመና ቅስቀሳቸውን እያካሄዱ ይገኛሉና። በዚሁ ሰይጣናዊ የፕሮፖጋንዳ  ብልሃት ሳትደናገር እንዳለፈው የስርዓቱን ተንኮል ለማኮላሸትና የስልጣን እድሜያቸውን ለማሳጠር ከሁሉም ጭቁንወች   በመተባበር ትግልህን አጠናክረህ እንድተቀጥልበት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴ.ን / ጥሪውን ያቀርባል።  
በጭቁን ህቦቻችን ላይ የተጫነውን የጭቆና ቀንበር በጋራ ትግል ይፈታል!!
ድል ለጭቁኖች!!
የትግርይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ት.ህ.ዴ.ን)