Friday, February 13, 2015

የደምቦያ ወረዳ ነዋሪ ህዝብ በደህዴን-ኢህአዴግ እየደረሰበት ያለውን አስተዳደራዊ ግፍ ለመቃወም ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።



ምንጮቻችን ከወረዳዋ  እንደገለፁት በደቡብ ክልል ከንባታ ጠንባሮ ዞን ደምቦያ ወረዳ የሚገኝ ህዝባችን በከተማዋ የሚገኘው መንገድ የተበላሸ እንደሆነና በተለይ ደግሞ በክረምት ወራት በጎርፍ ተጠቂ እንደሆነች ከገለፁ በኋላ በተደጋጋሚ ለመንግስት አቤቱታቸውን አቅርበው እስካሁን አወንታዊ ምላሽ ባለማግኘታቸው ምክንያት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ፊርማ በማሰባሰብ ስራ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።
መረጃው አክሎ የደምቦያ ወረዳ ነዋሪዎች የተበላሸው መንገድ ይሰራልን በማለት ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ሰዓት ከፈለጋችሁ ገንዘብ አዋጣችሁ እራሳችሁ አሰሩት ያሏቸው ሲሆን ስርዓቱ ግን የህዝቡን አቤቱታ ወደ ጉን በመተው የምርጫ ካርድ ውሰዱ እያላቸው የሚገኝ ሲሆን ህብረተሰቡ በበኩሉ አቤቱታችን መፍትሄ ካልተደረገበት የምርጫ ካርድ አንወስድም በማለት እንደመለሰላቸው ሊታወቅ ተችሏል።