በተለያዩ የሃገራችን ዩኒቨርስቲዎች እየተማሩ ያሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
መደበኛ ትምህርታቸውን ከመከታተል ይልቅ ስለመጪው አስመሳይ ምርጫ ላይ ያተኮረ የስርዓቱ ካድሬዎች በግዴታ እያስተማሯቸው እንዳሉና
የምርጫ ካርድም እንዲወስዱ እያስገደዷቸው እንደሚገኙ የገለፀው ይህ መረጃ ተማሪዎች በበኩላቸውም እኛ የመጣነው አካዳሚ ትምህረት
ለመማር እንጂ የኢህአዴግን ፖለቲካ ልንማር አይደለም በማለት ተቃውሞአቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ መረጃው አስርድቷል።
ስርዓቱን በሚያሞጋግሱ ፖለቲካ ላይ የተሰማሩ ደግሞ አንዳንድ ካድሬዎችና
ኢህአዴግን የሚወክሉ መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ ለዚህ መደበኛ ላልሆነውና ለአንድ ስርዓት የሚደግፍ ፖለቲካዊ ትምህርት ከሚጠቀሙ
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውስጥም የአዲግራት ዩኒቨርስቲና በአዲስ አበባ
የአራት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።