Sunday, February 1, 2015

በትግራይ ክልል የስርዓቱን ምስጢር ያውቃሉ የሚባሉ ንፁሃን ዜጎችን የማፈኑ ተግባር በህወሃት ካድሬዎች ተጠናክሮ መቀጠሉን ከትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ምንጮቻችን አስታወቁ።



 በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ተወላጅ የሆነው  ፀጋይ ታረቀ የተባለ ወገን ለ7 ዓመታት ያህል በእስር ቤት ቆይቶ አሁን ደግሞ ጥር 5 ቀን 20007 ዓ/ም በስርዓቱ ካድሬዎች ታፍኖ አድራሻው እንደጠፋ ለማወቅ ተችሏል።
 በመታፈኑ ምክንያትም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የዞኑ ፖሊስ ምክትል አዛዥ የሆነው ኮማንደር ግደይ የተባለ ካድሬ በ2002 ዓ/ም በእንዳባጉና የፖሊስ አዛዥ በነበረበት ወቅት ሰለሞን ገብረሰለማ ለተባለው ዜጋ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተኩል ከእስር ቤቱ አውጥቶ እንደሰወረው የገለፀው መረጃው አሁንም ፀጋይ ታረቀ ለተባለው ንፁህ ዜጋ በጊዜው ከእርሱ ጋር ታስሮ ቆይቶ ጊዜውን ጨርሶ በዚህ ሰሞኑን እንደወጣ  ለሰለሞን ገብረሰለማ ኮማንደር ግደይ የተባለው ፖሊስ በሌሊት አውጥቶ እንደወሰደው ለሰለሞን ቤተሰቦች በመናገሩ ምክኒያት የፖሊስ አዛዡ  በሰለሞን ቤተሰቦች መጠየቅ ስለጀመረ ያየው እንዳይመሰክር የሰጉ የዞኑ የፖሊስ አዛዦች ፀጋይ ታረቀን አፍነው እንደወሰዱት ሊታወቅ ተችሏል።