ከመከላከያ ሰራዊት የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው
ከሁሉም ክፍለ-ጦሮች የተውጣጡት 6 ወር የሚቆይ የመኮንኖች ግምገማ ጥር 14 2007 ዓ/ም መጀመሩና የግምገማው ዋና አጀንዳም ሰራዊቱ
በብዛት ለምን ይጠፋል የሚል እንደሆነ የገለፀው መረጃው የሰራዊቱ የመጥፋት ምክንያት ለዓመታት እየተነሳ የቆየው ማህበራዊ ችግር
መፍትሄ ስላልተደረገለት በዛው ልክ በስርአቱ ላይ እምነት አጥተው በየሄዱበት እንዲቀሩ ምክንያት ሆኗል ሲሉ የበታች መኮንኖቹ መናገራቸው
ታውቋል።
መረጃው በማስከተል የበላይ መኮንኖቹ የቀረበውን ችግር ላለመቀበል ብለው ወታደሮቻችን
እየጠፉ ያሉ የበታች አመራሮች በሚያደርጉት የአያያዝ ችግር ነው ተብሎ ቢገለፅም ከሻንበል በታች የሆኑት አመራሮች ግን እናንተ የሰራዊቱን
ችግር መፍትሄ ማድረግ ካልቻላችሁ እኛ እስረን የምንይዘው ሰራዊት አይኖርም በማለት ጥያቄ ማቅረባቸውና ስብሰባውም እየቀጠለ መሆኑን
መረጃው አክሎ አስረድቷል።