በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በነዋሪው ህዝብ
መካከል ውህደትና እሰት ተብለው በሚጠሩ የትግራይና
የዓፋር ቀበሌዎች ባለፈው መስከረም ወር ተከስቶ በነበረው ግጭት ስልጣን ላይ ያለው ገዢ ስርዓት ትኩረት ባለማድረጉ ከ10 በላይ
ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን የገለጸው መረጃው በስርዓቱ ካድሬዎች ለምርጫ ተመዝገቡና ካርድ ውሰዱ በሚባሉበት ሰዓት በኢህአዴግ ስር
ህጋዊ ምርጫ ብሎ ነገር ስለሌለ ማንን ለመምረጥ እንመዘገባለን በማለት መቃወማቸውን የተገኘውን መረጃ አስታወቀ።
በህብረተሰቡ ተቃውሞ የተናደዱት የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች ለአፅቢ
ወንበርታ ወረዳ የውህደት ቀበሌ የሆኑትን ነዋሪዎች በስብሰባ ምክንያት ከቀን ስራቸው እያስተጓጎልዋቸው ቢሆኑም ህዝቡ ግን ዛሬ ይሁን
ነገ ዋስትና ለማይሆነን ድርጅት አንመርጥም፤ ከኢህአዴግ ውጭ ለሆኑ ድርጅቶች ለመምረጥም እድል ስለማናገኝ አንመዘገብም በማለት የቀረበላቸውን
ቅስቀሳ እንደተቃወሙት መረጃው አክሎ አስረድቷል።