Sunday, February 1, 2015

ለአስመሳዩ የህወሃት ኢህአዴግ ምርጫ ግምት ውስጥ ያላስገባው የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ህዝብ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ እየተገደደ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።



   የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ህዝብ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ  በገዥው ስርዓት አስተዳድሪዎችና ካድሬዎች ጠንካራ ቅስቀሳ እየተደረገለት ቢሆንም ከህወሃት ኢህአዴግ ምርጫ ለውጥ እንደማይገኝ ካለፉት ምርጫዎች ስለተረጋገጠ ለህወሃት ኢህአዴግ የምርጫ  ቅስቀሳ ግምት ሳይሰጥ በማህበራዊ እንቅስቃሴው ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየተንቅቀሳቀሰ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አስታውቀዋል።
   በህብረተሰቡ ጠንካራ እርምጃ መጥፎ ስሜት ውስጥ የገቡ የስርዓቱ ባለስልጣናት በጉጅሌና ብሎክ ህላፊዎች ተጠቅመው የእያንዳንዱን ነዋሪ ህዝብ በር በማንኳካት ለህብረተሰቡ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ እያስፈራሩት እንደሚገኙ ታውቋል።
   በመቐለ ከተማ የስርዓቱ ካድሬዎች ከለፉት ምርጫዎች በበለጠ በየአካባቢው የምርጫ ጣቢያዎችን ሰርተው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው ይህ ደግሞ ላዘጋጁት አስመሳይ ምርጫ ማን የምርጫ ካርድ ወሰደ አልወሰደም በጥብቅ ለመቆጣጠር እንዲያስችላቸው በማሰብ የተጠቀሙበት መላ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድቷል።