በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማና
አካባቢው የሚኖር ማህበረሰብ በስርዓቱ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የገለፀው ይህ መረጃ። ታማኝ ተብለው
መሳሪያ ታጥቀው ሲያገለግሉ የቆዩ ነባር አባላት። ልጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የተቃዋሚ ድርጅት አባላት ሁነው
ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት በመቃወም እንቅስቃሴ በማካሄዳቸው። የያዙት መሳሪያ በአስተዳዳሪዎቹ እየተቀሙ መሆናቸውን
በአካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተፈራ ማሞ የተባለ ግለ ሰብ ከቅንጅት ድርጅት ጋር
አባል በመሆን እየሰራ በመሆኑ ደስታ ያልፈጠረላቸው የስርዓቱ ካድሬዎች የያዝከውን መሳሪያ ለመንግስት አስረክብ በማለት በቀሙበት
ሰዓት። ስዩም ማሞ የተባለው ወንድሙ መጋቢት ወር ላይ በተካሄደው ስብሰባ እናንተ ድሮውም ለህዝብ ልትጠቅሙ አልመጣችሁም ብሎ በመናገሩ።
በላሊበላ ከተማ በቀበሌ 02 በሚገኘው እስር ቤት ታስሮ እየተሰቃየ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል፣