Friday, April 17, 2015

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላምና ቡሬ ዳሞት የሚገኝ ህዝብ። ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.ን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳደረገ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት በምእራብ ጎጃም ዞን የፍኖተሰላምና የቡሬ ዳሞት ነዋሪዎች በስርዓቱ አስተዳዳሪዎች ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸውና ብ.አ.ዴ.ን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ምረጡ እየተባሉ እያሰፈራሯቸው በመሆኑ። ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን በተለይ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ሊመርጡ ይችላሉ ያሏቸውን ነዋሪዎችን በደህንነት አባላትና በፖሊሶች በሌሊት ከመኖሪያ ቤታቸው እያፈኑ  እያጠፏቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣
    መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ/ም በደህንነት አባላት በሌሊት ታፍነው ከተወሰዱት የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል።- አቶ ምናለ ሽፈራው፤ አቶ ታያቸው፤ አቶ አስረስና ሌሎችም ሲሆኑ በአካባቢው የሚገኙ ታጣቂዎችን ደግሞ ምርጫን አስመልክቶ ቅስቀሳ የሚያደርግ ከመጣ በጥይት በሉት የሚጠይቃችሁ አካል የለም በማለት ውስጣዊ ትዕዛዝ እንደሰጧቸውና ለመንቀሳቀሻ የሚሆን ገንዘብም እንዳሰጧቸው ለማወቅ ተችሏል፣