ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት የኦሮሞ ተወላጆች
በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚታየውን በርካታ የማህበራዊ ችግር የሚፈታ የአስተዳደራዊ አካል የለም በማለት ተቃውሞ ሲያስነሱ በስርዓቱ
የተደለሉ የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች የመማር ማስተማር ስራችንን የሚያደናቅፈን ነገር የለም ጥሩ አለን በማለት አንፃራዊ ሃሳብ
በማቅረባቸው የተነሳው ግጭት። መጋቢት 2 ቀን 2007 ዓ/ም በሌሊት ሁለት ተማሪዎች በስለት ተወግተው ሲገደሉ በርካታ ተማሪዎች
ደግሞ እንደቆሰሉ ለማወቅ ተችሏል፣
ይህ በሁለቱ
ክልል ተወላጅ ተማሪዎች መካከል የተለኮሰው ግጭት በዩንቨርስቲው ውስጥ በሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች ሆን ተብሎ የተያያዘ መሆኑን የገለፀው
መረጃው ይህንን ግጭት አግባብቶ መፍትሄ መስጠት የሚችል አካል ባለመኖሩ በመካከላቸው ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፣