በመረጃው መሰረት። የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
በውስጣቸው ባለው ብልሹ የአስተዳደር ሁኔታ የተነሳ። በአስከፊ የማህበራዊ ችግር ውስጥ ስለሚገኙ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ። ትልቅ
እንቅፋት እየፈጠረባቸው የሚገኝ ሲሆን። በተለይ የሚቀርበው ዳቦ ጥራቱን ያልጠበቀ፤ የዳቦው መጠንም የወረደና ምንም አይነት ይዘት
ከሌለው እንዲሁም ከተበላሸ እህል ስለሚሰራ ተማሪዎቹ ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆናቸው ተገልጿል፣
በማህበራው ኑሮ እጥረት እየተሳቀዩ የሚገኙት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች።
መፍትሄ እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ ያቀረቡት ጥያቄ ሰሚ ጀሮ ስላጣ። የተቃውሞ አድማ ለማካሄድ ዝግጅት ባደረጉበት ጊዜ። ሊካሄድ
በታሰበው ተቃውሞ ስጋት ላይ የወደቁ የስርአቱ ካድሬዎች። ትንሽ ጠብቁን እናሻሽለዋለን የሚል የማደናገርያ ቃል ቢያቀርቡም። የተማሪዎቹ
ስሜት ግን በመጥፎ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣