Thursday, April 16, 2015

በደቡብ ክልል ህዝቦች የሚገኙ መምህራን በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ደጋፊዎች አይደላችሁም በሚል በጥርጣሬ አይን እየታዩ ከፍቃዳቸው ውጭ ደመወዛቸውን እየቀነሱባቸው እንዳሉ ታወቀ፣



     በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በደቡብ ህዝቦች ክልል ቤንች ማጂ ዞን፤ ሰሜን ቤንች ወረዳ ዋቻ ማጂ ቀበሌ የሚገኙ መምህራን። ከተቃዋሚ ፓርቲ አባላትጋር ትሄዳላችሁ በሚል ሰበብ። በሃላፊዎቻቸው ክትትል እየተደረገባቸውና የደህዴን/ኢህአደግ ድርጅት የአባልነት ክፍያ አልከፈላችሁም እየተባሉ ከወር   ደመወዛቸው  እየተቆረጠባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣
     መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው። ከመምህራኑ አንዱ ማትዮስ ጋታሳብ የተባለ ወገን። መጋቢት 21/ 2007ዓ/ም የሃሰት ክስ በመመስረት ለ3 ወር ያህል ከደመወዙ 10 ከመቶ ተቆርጦ ወደ ድርጅት እንዲገባ በት/ቤቱ ርእሰ መምህር ትእዛዝ የተወሰነ ሲሆን። መምህሩ ግን ውሳኔውን እንዳልተቀበለውና እስከ አዲስ አበባ ት/ሚኒስተር  ድረስ በመሄድ ብሶቱን ለማሰማት በዝግጅት ላይ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣