በደረሰን መረጃ መሰረት ፓምሌቱ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች ማለትም መገናኛ አደባባይና በየከተማ አውቶቡስ
ፌርማታዎች ላይ እንዲሁም ቃሊቲ መናሃሪያ አካባቢዎችና መንገዶች ላይ የተበተነ ሲሆን የትህዴንን የተለያዩ አቋሞችና የገዥውን መንግስት
አፈናና ጭቆና በተመለከተ የሚገልፅ ሲሆን በሰላማዊ ትግል ምንም ዓይነት
የዲሞክራሲ ለውጥ ሊመጣ እንደማይችልና ዜጎች መብታቸውን ማስከበር ያለባቸው ወያኔ የሚመካበትን አፈሙዝ በማቅናት የትጥቅ ትግልን
በማጠናከር መሆኑን በአንክሮ የሚያስረዳ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም የተበተነው በራሪ ወረቀት የገዥውን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስትን የስልጣን እድሜ ለማሳጠር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወጣት
ትህዴንን በመቀላቀል የበኩሉን አስተዋፆ ማበርከት እንዳለበት ድርጅቱ ጥሪውን አስተላልፏል።