Sunday, May 17, 2015

የመቐለ ከተማ ህዝብ በስርዓቱ የፀጥታ አካላት እየተገደደ በስብሰባ ተጠምዶ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



   እንደምንጮቻችን መረጃ መሰረት በስርዓቱ የፀጥታ አባላት ከመኖሪያ ቤቱ እየተገደደ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኘው ነዋሪው ህዝብ እለታዊ ስራውን እያቋረጠ በስብሰባ ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው ስብሰባው ከሚያዝያ 25 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለአንድ ሳምንት የቆየ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
   የስብሰባው ዋና አጀንዳም ልማት እንዲቀጥል ከታሰበ በሚመጣው ምርጫ አጠቃላይ ህዝቡ ህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን መምረጥ እንዳለበት፤ ማንኛውም ሰው መኖሪያ ቤት ሲከራይ ያለመታወቂያ ካርድ ማከራየት እንደሌለበት፤ በከተማችን ውስጥ በጥርጣሬ አይን ለሚታይ ሰው ይዞ መጠየቅ እንዳለበት፤ የሆነ ንብረት አስቀምጡልኝ ለሚል ሰው ሳይፈትሽ ማስቀመጥ እንደሌለበት የሚሉና ሌሎችም መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።