Saturday, May 16, 2015

የሓረር ከተማ ህዝብ በመብራትና ሌሎች አላቂ እቃዎች እጥረት ምክንያት ማህበራዊ ኑሮውን መምራት እንዳልቻለ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የሓረር ከተማ ነዋሪ ህዝብ በመብራትና ሌሎች አላቂ እቃዎች እጥረት ምክንያት እየተሰቃየ መሆኑና በተለይ ካለፈው ሚያዝያ ወር 2007 ጀምሮ በከተማው ውስጥ የመብራት አገልግሎት ፈፅሞው የማያገኙ አካባቢዎች መኖራቸውን የገለጸው መረጃው ህዝቡ እለታዊ ኑሮውን ለመምራት በመቸገሩ ምክንያትም የእስልምና አምነት ተከታይ የሆኑ አባቶች ምሽት ላይ ወደ መስጊድ በሚሄዱበት ሰዓት ሞባይላቸውንና ገንዘባቸውን በሌቦች እየተነጠቁ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
     በሃረር ከተማ በመብራት አገልግሎት እጥረት እየተሰቃዩ ካሉት ቦታዎች ለመጥቀስ ያህል ሸዋ በር፤ ቡዳ በርና ሌሎች አካባቢዎች መሆናቸውንና የክልሉ መሪዎች ግን እስካሁን ድረስ ለችግሩን መፍትሄ ማድረግ እንዳልቻሉ፤ በተጨማሪም በከተማው ውስጥ እንደ ዘይት፤ የፊኖ ድቄትና የመሳሰሉት ነገሮች ከጠፉ ወራቶች ማስቆጠራቸውን የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።