Saturday, May 16, 2015

በደቡብ ክልል በሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ ተመዝግበው ምርጫ የሚወዳደሩ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት በኢህአዴግ የፀጥታ አባላት በመታሰር ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።



ምንጮቻችን ከአካባቢው እንደገልፁት በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ሚዛን ተፈሪ ከተማ በሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ኢህአዴግ በገንዘብ አታልሎ ባቋቋማቸው የሃሰት መስካሪዎች በላያቸው ላይ የሃስት ምስክር እንዲመሰክሩ በማድረግ ባልዋሉበትና በማያቁት ወንጀል ስማቸውን እያጠፋ በማሰር ስራ ላይ እንደሚገኝ የገለፀው ይህ መረጃ፣ ከታሰሩት ውስጥም አንዱ መምህር አበበ ይልማ የተባለ በከተማዋ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለሆነው ዜጋ ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት አለህ ተብሎ ሚያዚያ 18 2007 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ ተይዞ በቤንች ማጂ እስር ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችኋል።
   የደረሰን መረጃ አክሎ እንደገለፀው ይህ በሰማያዊ  ፓርቲ አባላት ላይ እየወረደ ያለው የማሰርና የማንገላታት ተግባር በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት አጠናክሮ እየቀጠለበት እንደሚገኝ ታውቋል።  

`