በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት ታጣቂዎች ግንቦት 12
/2007 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የእጅ ቦምብ በመወርወር በበርካታ ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት እንዳደረሱ የገለፀው
መረጃው ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ ጓንቲን ደርቤ የተባለችና 4 የዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች እንዲሁም ሌሎችም የሚገኙባቸው
እንደሆኑ ሊታወቅ ተችሏል።
እነዚህ ታጣቂዎች ይህ የተተኮሰው ቦንብ ከተቃዋሚ ድርጅቶች የተተኮሰ ነው
ብለው ለማደናገር ቢሞኩሩም ተማሪዎቹ ግን ይህ ከተቃዋሚዎች ሳይሆን እራሳችሁ ሆን ብላችሁ ያደረጋችሁት ነው። በዚህ አካባቢ ተቃዋሚዎች
ከነበሩ ለምን አትዩዟቸውም በማለት ለእኩይ ተግባራቸው በግልፅ እንደነገሯቸው ታውቋል።
ከከተማዋ ሳንወጣ ጠቅላይ ሚንስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ግንቦት 10/
2007 ዓ,ም ወደ ነቀምቴ ከተማ በመሄድ አዲስ የአየር ማርፊያ ለማሰራት የመሰረተ ድንጋይ ለማስቀመጥ በሞከረበት ሰዓት የከተማዋ
ህዝብና ተማሪዎች ግን ቅንነት የሌለው ለምርጫ ሲባልና ህዝቡን ለማታለል ተብሎ የሚደረግ እንጂ ምርጫው ካለፈ በኋላ የሚቀጥል አይደልም ስለዚህ ወደዚህ ቦታ እንዳይገባ
በማለት የተቃውሞ ሰልፍ ባካሄዱበት ሰዓት የነበረው ተቃውሞ በታጣቂዎች ሃይል እንዲበተን እንዳደርጉ ሊታወቅ ተችሏል።