Wednesday, June 3, 2015

የተዳከመውን የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለማጠናከር ሲባል በ1993 ዓ,ም የተባረሩት አመራሮች እንዲመለሱ መስማማታቸውን ምንጮቻችን ገለፁ።



የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመለስ ሞት በኋላ ውስጣዊ አቅማቸው ተዳክሞ እየተንገዳገዱ ቢቆዩም በዚህ ሰዓት ግን ህልውናቸው በስጋት ላይ ወድቆ ስለሚገኝና ከውድቀታቸው ለመነሳት የሚያስችል አቅም እንደሌላቸው ስለተረዱ በ1993 ዓ.ም ላይ የድርጅቱ አላማ የሚፃረሩ  ናቸው፤ በህዝባችን ላይም ከፍተኛ በደል ፈፅመዋል በማለት አባረዋቸው የቆዩ የድርጅቱ ማዕከልዊ ኮሚቴ አባላት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ባደረጉት ጥረት ስምምነት ላይ እንደደረሱ ምንጮቻችን አመለከቱ።
     ከአመራርነት ተባርረው የቆዩ የህወሃት አመራሮች የነበሩና አሁን እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ደርሰዋል የተባሉት ሰዎች  ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገብረተንሳኤ፤ ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ) አረጋሽ አዳነ፤ አውዓሎም ወልዱና ተወልደ እውር ሲሆኑ በእርቅ ስምምነቱ ላይ ሌተናል ፃድቃን ገብረተንሳኤ ያለምንም ጥፋት አባራችሁን ስለቆያችሁ ካሳ ይሰጠን የሚል ሃሳብ ማቅረቡ የገለጸው መረጃው አብዛኛዎቹ የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴዎች በተነሳው ሃሳብ ላይ የተስማሙ ሲሆን ጥቂቶቹ ግን ጥያቄውን እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል።
     በማስታረቅ ስራ ላይ ተጠምደው የሰነብቱት ሰዎች ደግሞ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፤ አርከበ ዕቑባይ፤ በረከት ሰምኦንና አዲሱ ለገሰ መሆናቸውና ገብሩ አስራት ግን የህወሃት ኢህአዴግን ድርጅትና አመራሮች የሚያዋርድ ታሪክ ስለፃፈ መመለስ የለበትም ብለው እንደተስማሙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።