ህወሃት/ ኢህአዴግ በሰማእታት ስምና በጀግኖች ሰማእታት ቤተሰቦች እየነገደ
በራሱ ጥቅም አስተሳሰብ ብቻ ተጠምዶ መንቀሳቀስ ከጀመረ እንሆ 24 ዓመታት አስቆጥሯል።
የህወሃት/ማሌሊት ካድሬዎች በየአመቱ ሰኔ 15 ቀን በትግራይ ክልል ደረጃ
የሰማእታት ቀን ብለው በመዘከር የአዞ እንባ ቢያነቡም ሃቁ ግን አስመሳይነታቸውን ይበልጥ አጉልቶ ያሳየና፣ በተለይ ለትግራይ ህዝብ
ባጠቃላይ ደግሞ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ አፍነውና አደናግረው ለመያዝ እየተጠቀሙበት ያለ ብልሃት መሆኑ ሲበዛ ግልፅ ነው።
የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ወደ ትግል መርቆ ሲልክ፣ በላዩ ላይ የጭቆናው
ግፍ ሲፈፅም የነበረውን ፍሽስታዊ የደርግ ስርዓት አስወግዶ ከኢትዮጵያ
ብሄር ብሄረሰቦችበ ጋር መብቱ ተከብሮለት ብሰላም አብሮ ለመኖርና
ኮርቶ የሚኖርባት አገር ለማየት ከነበረው ፍላጎት ነበር፣ ነገር ግን በህወሃት ማሌሊት ከሃድያን አመራሮች ምኞቱ ሊሳካ አልቻለም።
ህወሃት ማሌሊትና ስርአቱን የሚመሩት የበላይ ባለስልጣኖች፣ የህዝብና የሃገር
ገንዘብ በመዝረፍ ያሰባሰቡት ሃብት ተጠቅመው ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው ሲፈነጥዙበት፣ የሰማእታት ወላጆች ግን ደጋፊና ጧሪ አጥቶው በከፋ
ችግር ስኖሩ በሰማእታት ደም እየነገዱ ያሉት ባለስልጣኖች ግን በተጓዳኝ፣
በምንም ዓይነት ድንጋጤ አልተሰማቸውም ብቻ ሳይሆን፣ በሰማእታት ላይ ያላቸው ክዳትና ጭካኔ በሚያሳዝን ሁኔታ እየቀለዱ ይኖራሉ።
ህወሃት/ኢህአዴግ ባለፈው ግንቦት 16/2007 ዓ/ም ያካሄደው ፍፁም ፍትሃዊ
ያልሆነ ምርጫ፣ “ዝሆን ቂጡን ተማምኖ ግንድ ይውጣል እንደሚባለው ” የስርዓቱ መሪዎች በሚያወርዱት ቀጥታዊ ትእዛዝ፣ በንጹሁ ህዝብ
ላይ ታጣቂዎቻቸው የተለያዩ ተፅእኖዎች፤ ድብደባና የመግደል እርምጃዎች እየወሰዱ ባሉበት ግዜ፣ የተካሄደውን አስመሳይና የተጭበረበረ
ምርጫ፣ የሰኔ 15 የሰማእታት ቀን ውጤት ነው ማለታቸው፣ አሁንም ባገራችን ውስጥ እውነተኛው የዴሞክራሲ ስርዓት ለማምጣት ብለው
ውድ ህይወታቸውን በከፈሉ ሰማእታት ላይ መቀለድ ከመሆን አልፎ፣ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው አይደለም።
ፀረ ህዝብ የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት ባለፉት
24 የአገዛዝ ስልጣኑ፣ የመፃፍ፤ የመናገርና የመደራጀት መብት መከልከሉ፤ በተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮችና አባሎቻቸው ላይ
አሰቃቂ በደሎች እየፈጸመ በሚገኝበት ወቅት ዴሞክራሲ ለመገንባት ጥረት እያደረግን ነን ቢልም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ፍትህና መልካም
አስተዳደር ማየት አልቻለም ብቻ ሳይሆን፣ እስከ አሁንን የተካሄደውን አስመሳይ ምርጫ በጠበንጃ አፈሙዝ ታጅቦና የተለያዩ ተንኮሎች
ተዘጋጅቶበት የንፁሃን ዜጎወቻችንን ደም የፈሰስበትን ፍፁም ኢ-ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለተገባደዱት በሰማእታት ቀን ሰኔ 15
ለመነገድ እንደማይችል መታወቅ አለበት።