በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በመቱ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደውን ምርጫ አብዛኛዎቹ
ተማሪዎች ለተቃዋሚ ድርጅቶች መምረጣቸውን የተረዱት የስርዓቱ ካድሬዎች የምርጫው ኮረጆ ሰርቀው በመቀየር ኢህአዴግ 1568 አብላጫ
በማግኘት አሸንፈዋል በማለት ግንቦት 17/ 2007 ዓ/ም ይፋ ያደረጉትን ውጤት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ስላልተቀበሉት ዓመፅ ማካሄዳቸው
ታወቀ።
በምርጫው ጣብያ ኢህአዴግን በትክክል የመረጠ 168 ሰው ብቻ እንደሆነ፤
የቀሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ግን ለተቃዋሚዎች ስለመረጡ ገዢው
ስርዓት ሙሉ በሙሉ መሸነፉን የገለፀው መረጃው ሁኔታውን የተረዱት የስርዓቱ አስተዳዳሪዎች ታጣቂዎች በማሰማራት ድምፃችን ተሰርቋል
ብለው ተቃውሞ ባስነሱት ተማሪዎች ላይ ቶክስ በመክፈት ከ100 በላይ ተማሪዎች ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ማድረጋቸውና የቀሩትም ከትምህርት
ገበታቸው አቋርጠው በመሸሻቸው ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዳቋረጠ ለማወቅ ተችሏል።