Saturday, July 18, 2015

በዓዲ-ግራት ከተማ በሰው ህይወት ላይ የሚደርሰው የመኪና አደጋ። የትራፊክ ፖሊስ በቸልተኝነት ስለሚመለከቱት ነዋሪው ህዝብ እያማረረ መሆኑን ተገለፀ።



     በመረጃው መሰረት ብምስራቃዊ ዞን፤ በዓዲ ግራት ከተማ የሚገኙ የትራፊክ አባላት ሃላፊነታቸው በተገቢ መንገድ ስለማይፈፅሙ በተሽከርካሪዎች የሚደርሰው አደጋ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መሆኑን የገለፀው መረጃው በዚህም ምክንያት ሓምሌ 2/2007 ዓ/ም በ05 ቀበሌ አካባቢ ለአንድ ልጅ በመኪና ገጭቶ የገደለው ሾፌር ተከታትሎ የሚይዝ የፖሊስ ትራፊክ ባለመኖሩ እስካሁን ወንጀለኛው መያዝ እንዳልተቻለ ለማወቅ ተችሏል።
     የተገኘው መረጃ በማስከተል የፖሊስ ትራፊክ አባላቱ ወንጀሉን ለመከላከልና አደጋ የሚያደርሱትን ባለ አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ዓቅም አጥተው ሳይሆን ከሾፌሮቹ ጉቦና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች በመቀበል የግል ህይወታቸው በማሳደግ ብቻ  በመጠመዳቸው የተፈጠረ ችግር መሆኑን የአካባቢው ህዝብ በምሬት መግለፁን የተገኘው መረጃ አስታውቋል።
     ይህ በንዲህ እንዳለ የስርዓቱ አገልጋዮች የሆኑ የወታደራዊ ተሽከርካሪ ሹፌሮች በህዝቡ ላይ ግፍ በሚፈፁምበት ግዜ ጠያቂ አካል እንደሌላቸው የገለጸው መረጃው ሰኔ 30/2007 ዓ/ም ነዋሪነቱ ዓዲግራት 04 ቀበሌ የሆነው መምህር መዝገበ የተባለ ግለሰብ በወታደራዊ ኦራል ተሽከርካሪ መኪና ተረግጦ ለማወቅ ተችሏል።
    ይህ የሰው ህይወት ያጠፋውን ወታደር በህግ ፊት የሚያቀርበው አካል እንዳልተገኘና በዚህ አስነዋሪ ተግባርም የከተማው ነዋሪና የተጎጂው ቤተሰብ በስርዓቱ ላይ ቅሬታቸውን በማሰማት እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።