Monday, July 6, 2015

ባሳለፍነው ሳምንት ከተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች፣ በርካታ ወጣቶች፣ ህወሃት ኢህአዴግን በመቃወም ወደ ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ መቀላቀላቸው ከትህዴን ማሰልጠኛ ክፍል ወኪላችን አስታወቀ።



     በህዝባችንና በሃገራችን ታሪክ ይቅር የማይለውን ግፍና በደል እየፈፀመ ያለውን ፀረ ህዝብ ስርዓት ማስወገድ የሚቻለው በትጥቅ ትግል ብቻ ነው በማለት ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ከተቀላቀሉት ጥቂቶቹን ለመግለፅ
1.   ጠዓመ አማረ ተስፋይ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን፤ ጉለመኸዳ ወረዳ፤ ሸዊት ቀበሌ፤ ቦቑሎ አካባቢ፤
2.   መብርሂት ረደሀኝ ገ/የሱስ፤ ከሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ክሳድ ገባ ወረዳ፤ ሕጻፅ ቀበሌ
3. ግርማይ ስእሉ ገ/ማርያም ከምስራቃዊ ዞን፤ ኢሮብ ወረዳ፤ እንዳልጌዳ ቀበሌ፤ መኸታ ቀበሌ፤
4.  ጉዕሽ ተኽሊት ሊበን፤ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ፤ ዓዲ ፍታው ቀበሌ፤ ዓዲ ሓንገደ አካባቢ፤
5.   ጋይም ወልደማርያም አብርሃ፤ ከምስራቃዊ ዞን፤ ኢሮብ ወረዳ፤ ዓሊቴና ቀበሌ፤ ዓይጋ አካባቢ፤
6.  ፀጋይ ፍሻለ አብርሃለይ፤ ከምእራባዊ ዞን፤ ዓዲ ዳዕሮ ወረዳ፤ ዕጉብ ቀበሌ፤ ዓዲ ርእሶ አካባቢ፤
7.  መለስ መሓሪ ሊባኖስ፤ ከሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ ዓዲ ክልተ ቀበሌ፤ ገዛ ስቓ አካባቢ፤
8.  ሓለፎም አረጋዊ ገብሩ፤ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ዓዲ ፍታው ቀበሌ፤ ዓዲ ሓንገለ አካባቢ፤
9.  አዳነ ታረቀ አበበ፤ ከአማራ ክልል፤ ሰቆጣ አበርጌለ ወረዳ፤ ቁጠብዋ ቀበሌ፤ አብደገን አካባቢ፤
10 ተኽሎም ብርሃነ ገ/ሚካኤል ከማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ መዳሎ ቀበሌ፤ ዓዲ ፍታው አካባቢ፤
11  መኮነን ገብረገርግስ፤ አማናኤል ግደይና አረጋዊ ገብርሂወት፤ ከማእከላዊ ዞን፤ ዓዲ ዓሕፈሮም ወረዳ፤ ዝባን ጒላ ቀበሌ፤ ጎላጉል አካባቢ የሚገኙባቸው እጅግ በርካታ ወጣቶች እንደሆኑ ወኪላችን ከትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል በላከው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
እላይ ከተገለፁት ባርካታ ወጣቶች ውስጥ መብርሂት ረደኸኝ እንደገለፀችው በወላጆቿ ሱቕ እየሰራች እንደነበረችና ባገራችን ያለው ቅጥ ያጣ የግብር አከፋፈል አስመልክታ በሰጠችው  ሃሳብ ላይ የንግድ ማህበረሰቡ የንግድ ወጪውና ገቢው በተጣራ መንገድ ጥናት ተደርጎበት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ግብር እንዲከፍል ስለማይደረግ፣ አብዛኛውን ነጋዴ ለኪሳራ ተጋልጧል ስትል አስረድታለች።
ወጣትዋ ሃሳብዋን በማከል አንድ ነጋዴ ግብር ሰብሳቢዎችን አስቀድሞ ግቦ ካልሰጣቸውና በጥቅም ሊግባባቸው ካልቻለ፣ የተለያየ መሰናክሎች በመፍጠርና ከአቅሙ በላይ የሆነ ግብር እንዲከፍል በማስገደድ ከስራው ተማሮ ለማቋረጥ እንደሚያስገድዱት ገልጻለች።
በከብት እረኝነት ተሰማርቶ ይሰራ የነበረውን ፀጋይ ፍሻለ በበኩሉም በርካታ ከእርሻና  ከእረኝነት ስራ የተያያዘ ሂወት እየመሩ የቆዩትን ዜጎቻችን ትጥቅና ስንቅ በማመላለስ ከትህዴን ጋር እየተባበራችሁ ነው በማለት እየታሰሩና የተለያየ ግፍ እየደረሰባቸው እንደሆኑ ገልጿል።
ግርማይ ስእሉና ጋይም ወለማርያም በበኩላቸው ዛሬ ባገራችን ውስጥ ትምህርት ጨርሰህ ስራ ማግኘት አይቻልም፤ ማንኛውም የመንግስት ስራም በግቦና በዘር አድልዎ ስለሚፈፀም አብዛኛው በሁኔታው ተማርሮ ወደ ስደት እያመራ ያለበት ሁኔታ እንደሆነ አስረድቷል።
በመጨረሻም ወጣቶቹ ወደ ስደት ማምራት የከፋ ችግር መፍጠር እንጂ ለችግራችን መፍትሄ ስለማይሆን መፍትሄው የትጥቅ ትግል ማካሄድ እንደሆነ አምነው ከትህዴን ጎን በመሰለፍ እንዲታገሉ መወሰናቸው አክለው አስረድቷል።