በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን፤ በእንደርታ
ወረዳ የሚገኙ አርሳደሮች ፍትሃዊ ባልሆነ ዋጋ ማዳበርያ ግዙ እየተባሉ በስርዓቱ ካድሬዎች እየተገደዱ መሆናቸው የገለጸው መረጃው
አርሳደሮቹ እስገዳጅ የሆነውን አካሄድ በመቃወም አቤቱታቸው ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ አጥተው መሬታቸውን እንዳያርሱ መከልከላቸውን ለማወቅ
ተችሏል።
መረጃው በማከል እርሶአደሮቹ የማዳበርያው ዋጋ ከምያገኙት ምርት ስለማይመጣጠን
ፍትሃዊ የሆነው አከፋፈል ይደረግልን ብለው ምሬታቸው ቢያሰሙም እስካሁን ድረስ ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ የሚሰጣቸው አካል እንዳላገኙ
መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።