የኢህአዴግ ስርዓት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሰኔ 15/2007 ዓ/ም ባለፈው
17 ዓመት የትጥቅ ትግል የወደቁትን ሰማእታት ለማስታወስ በሚል ምክንያት በአዲስ አበባ፤ የካ ክፍለ ከተማ ውስጥ ያካሄዱትን ስብሰባ
መድረኩን ይመሩ የነበሩት የስርዓቱ ካድሬዎች የጠሩትን የስብሰባ አላማ በመቶው ግንቦት 16/ 2007 የተካሄደውን የይስሙላ ምርጫ
አስመልክተው በዚህ ስብሰባ ላይ እኛን የመረጠና ያልመረጠ አንድ ጋር በመሰብሰብ ማነጋገራችን የዴሞክራሲ ስርዓታችን ውጤት ነው እያሉ
በመናገራቸው የተበሳጩ ተሰብሳቢዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ታወቀ።
በስብሰባው ላይ ከቀረበው ተቃውሞ ያለፉትን ሰማእታት እናንተ ሳትሆኑ
ለህዝብና ለሃገር ብለው የተሰው እውነተኛ የህዝብ ወገኖች ስለሆኑ በነሱ አትነግዱ፤ የተሰበሰብንበት አላማ አንስተን እንነጋገር እንጂ
ያለፈውን ምርጫ እያነሳችሁ እረፍት አታሳጡን በማለት አምርረው በመቃወማቸው። ስብሰባውን ያለ ምንም ፍሬ መበተኑን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በንዲህ እንዳለ አዲስ አበባ በሚገኘው ሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ አርከበ
እቁባይ በመራው ስብሰባ ላይ የሰማእታት ቀን በሆነችው ሰኔ 15 እለት ላይ ለሰማእታት ክብር ከመስጠት ይልቅ በግብዣ፤ በጭፈራና
ዳንኬራ እንዲያልፍ መደረጉ ተከትሎ የሰማእታት ቤተሰቦችና ያገባናል የሚሉ ሌሎች ዜጎቻችን ቁጣቸውን መግለፃቸውና መነጋገርያ አጀንዳቸው
እንዳደረጉት የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።