Friday, August 7, 2015

የሁመራ ከተማ ምክር ቤት ከሃምሌ 21 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ በአካሄደው ስብሰባ በርካታ የተቃውሞ ጥያቄዎች መነሳታቸው ሊታወቅ ተችሏል።



    በተጠቀሰው ዕለት የተጀመረውን  የሁመራ ከተማ ምክር ቤት  ስብሰባው ይመራው የነበረው የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሰለሙን አየነው ሲሆን በስብሰባው ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ስራችንን መስራት አልቻልንም ለምንስ ችግሩ የማይነገርና መፍትሄ የማይሰጠው? ከፍተኛ አመራሮች በከተማችን እየገቡ ግጭቶች እንዲነሱ ምክንያቶች እየሆኑ ናቸው ችግሮችንስ ለምን እንዲባባሱ ይደርጋሉ የሚሉና ሌሎችም መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
    በተጨማሪም ለከተማዋ አጠቃላይ መንገዶች ለኮብልስቶን መስሪያ ተብሎ በጀት ተመድቦ እያለ ስራው ግን በመናኸሪያ ብቻ ነው እየተሰራ ያለው ስለዚህ ለከተማዋ አጠቃላይ መንገዶች ተብሎ የተመደበውን በጀት የት አደረሳችሁት የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም  መድረክ መሪው አቶ ሰለሙን ግን ምንም ምላሽ እንዳልሰጠ ለማወቅ ተችሏል።