ምንጮቻችን ከአካባቢው እንደገለፁት፣ በአማራ ክልል፤ ሰሜን ወሎ ዞን፤ ስሪንቃ በተባለው ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች፣ ከዚህ
በፊት ከአረብ አገሮች የተመለሱ ሲሆኑ፣ መንግስት ማቋቋምያ ይሰጣችኋል በማለት ቃል የገባላቸው ቢሆንም፣ ወደ አገራቸው ከገቡ በኋላ
ግን እስካሁን ድረስ ማንኛውም የመንግስት አካል እዳልተከታተላቸው በዚሁ ተግባር ተስፋ የቆረጡት ወጣቶችም እንደገና ወደ አረብ አገሮች
ለመመለስ በመኮሩበት ሰዓት፣ መንገድ ላይ ተይዘው በሃሰት ምስክርነት የሰዎችን ህገወጥ አሸጋጋሪዎች ናችሁ ተብለው ወልድያ ከተማ
ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ስርዓቱ በኢትዮጵያ ህዝብ ፊት ለራሱ መልካም አተሳሰብ እንዳለው መስሎ
ቢቀርብም፣ እገዛ እንደሚያደርግላቸው የገባላቸውን ቃል ተግባር ላይ ባለመዋሉ ምክንያት ተስፋ ቆርጠው ወደ ስደት መሄድ በጀመሩበት
ሰዓት ሓምሌ 5/2007 ዓ/ም በፌደራል ፖሊስ አባላት ተይዘው ከታሰሩት መካከል፣- ወጣት ጣሂር እሸቴ፤ መሓመድ ዓሊ፤ ሬድዋን ያለውና
ዘምዘም ዳውድ የተባሉት የሚገኙባቸው በርካታ ወጣቶች መታሰራቸው የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።