በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ ንኡስ ወረዳ ዳዕሮ ሓፋሽና ማዕበረ በይንና አካባቢ
የሚኖረው ህዝብ በናዕዴር ዓዴት ወረዳ አስተዳዳሪዎች ከዓቅሙ በላይ በሆነና ተመጣጣኝ ባልሆነ ዋጋ ማዳበርያ እንዲወስድ እየተገደደ
መሆኑን የገለፀው መረጃው አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው ለማዳበርያ መግዣ የሚሆን ገንዘብ የለንም! በችግር ላይ ችግር አትጨምሩብን ባሉበት
ሰዓት በአስተዳዳሪዎቹ በኩል እንደዚህ ዓይነት መልስ የሰጠ መሬቱን ነጥቀን ከአካባቢው እናባርረዋለን እያሉ በማስፈራራት ላይ ተጠምደው
እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ህብረተሰቡ በአስተዳዳሪዎች ሊደርስበት የሚችል የማባረርና የማሰር እርምጃ
ስጋት ላይ ስለወደቀ ንብረቱንና ከብቶቹን በመሸጥ የቀረበውን ማዳበርያ ገዝቶ ለመውሰድ እየተገደደ መሆኑን ማንጮቻችን ከአካባቢው
ጨምረው አስረድተዋል።