በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ በታህታይ አድያቦ
ወረዳ፤ ዓዲ ጸፀርና አካባቢው የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ከብቶቻቸውን ይዘው በአካባቢው
ወደሚገኙ ነፃ መሬት በሄዳቸው ለግዜው መሬቱን አርሰው ሊጠቀሙ በሞከሩ አርሶአደሮች ላይ የወረዳውን ሚሊሻዎችና ሌሎችንም በማሰማራት
ሊያባርሯቸው በሞከሩበት ጊዜ በተነሳው ብጥብጥ ምክንያት፣ በአካባቢው ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
አርሶ አደሮቹ ቀደም ብለው በክረምት ወቅት ወደ አካባቢው እየሄዱ ከጥቅም
ውጭ የሆነውን የእርሻ ቦታ አርሰው እና ለከብቶቻቸው ግጦሽ እየተጠቀሙበት እንደነበር የገለፀው መረጃው፣ ዛሬ ደርሰው የአካባቢው
አስተዳዳሪዎች ይህን ያህል ትኩረት ሰጥተው የአካባቢያችንን መሬት ልቀቅሉን ማለታቸው አርሶአደሮቹን ክፉኛ ስላሳሰባቸው ከአገራችን
አልፈን ወዴት ልንሄድ ፈለጋችሁ በማለት ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በመካከላቸው መፍትሄ ያላገኘ ከፍተኛ ጠብ መፈጠሩን ምንጮቻችን
ከአካባቢው አክለው አስረድተዋል።