Wednesday, August 5, 2015

በአፋርና በትግራይ ክልል መካከል መሬትን መነሻ ያደረገ ግጭት በመነሳቱ ምክንያት ነዋሪዎች ከባድ ውጥረት ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙ ከአካባቢው የተገኘው መረጃ አመለከተ።



    በመረጃው መሰረት በዓፋርና በትግራይ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ የአፅቢና የበራህሌ ወረዳ ነዋሪዎች መሬትን መነሻ ባደረገ ግጭት መጠመዳቸውን የገለፀው መረጃው በዚህም መሰረት የአፅቢ ወረዳ ህዝብ መሬቱ የኛ ነው በማለት ገፍተው በመግባታቸውና በራህሌ ድረስ በመሄድ ሦስት ክላሽ ኮፕ ጠመንጃ ነጥቀው በማምጣታቸው ምክንያት ግጭቱ ይበልጥ መባብሱ ተገለፀ።
    መረጃው በማከልም በሁለቱም ክልሎች የሚገኙት ታጣቂዎች ውጥረት ባለበት አካባቢ ላይ ሓምሌ 18/2007 ዓ/ም ስለተሰባሰቡ እንዲሰበሰቡ ሁኔታው ወደተባባሰ ውጊያ እንዳያመራ ከፍተኛ ስጋት ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞችን መሰረት ያደረገ መረጃ አስታውቋል።