በትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ በሑመራ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ
ተድራጅተው በመናሃሪያና አካባቢ የሚገኘውን መንገድ ድንጋይ ለማንጠፍ በ2 ሚሊዮን ብር እንዲሰሩት ከከተማው አስተዳደር ውል ቢፈፅሙም
ሰርተው ከጨረሱ በኋላ ግን በገቡላቸው ውል መሰረት ገንዘቡን ሊሰጧቸው
እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችሏል።
የተሰራውን የድንጋይ ንጣፍ ውል የፈፀመው የከተማው አስተዳደር አቶ ጎይትኦም
አለማየሁ የተባለ እንደሆነ የገለጸው መረጃው ሰራተኞቹ የሰራንበት
ገንዘብ ስጠን ብለው በሚመላለሱበት ግዜ መስራቤቱ ውስጥ እያለ የለም በሏቸው በማለት ስለሚያጉላሏቸው መፍትሄ ለማግኘት ብለው ላይ
ታች እያሉ ቢሆንም የበላይ ባለስልጣናት ግን ብሶታቸውን ሰምተው እንዳልሰሙ ሆነው ዝምታ መምረጣቸው ባለስልጣኑ ከነሱ ጋር ሆኖ ገንዘቡን
አጠፋፍቶታል የሚል እምነት እንዳሳደረባቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።