Wednesday, August 5, 2015

የሸራሮ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች በመጡ የቀን ሰራተኞች በማጥለቅለቅዋ የከተማዋ የፀጥታ አካላት የማንነት መታወቂያ ካርድ አልያዛችሁምና አላሳደሳችሁም በማለት እያሰሩ ግፍ እየፈፀሙባቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽራሮ ከተማ  የክረምቱን መግባት ተከትሎ በአካባቢው በሚገኘው ሰፊ የእርሻ መሬት በቀን ስራ ለመስራት በየአካባቢያቸው የስራ ዕድል ሊያገኙ ያልቻሉ በርካታ ዜጎች በተለይ ተማሪዎች በጉልበታቸው ሰርተው ዕለታዊ ጉርስ ለማግኘት የተንቀሳቀሱ ሲሆን የከተማዋ ፖሊሶች በየመንገዱ እየጠበቁ የመታወቂያ ካርድ አልያዛችሁም ወይም አላሳደሳችሁም በሚል ሰንካላ ምክንያት እያፈሱ በማሰር እያባረሩዋቸው መሆናቸው ሊታወቅ ተችሏል።
   ግፍ እየተፈፀመባቸው የሚገኙ ወገኖቻችን በተወለድንበት ሃገር በፈለግነው ቦታ ተንቀሳቅሰን መስራት ካልቻልን ወዴት እንድንሄድ ፈልጋችሁ ነው በማለት ለተቃወሟቸው ወጣቶች በልዩ ሁኔታ እንደሚመለከቷቸው የገለፀው መረጃው ይህ በፀጥታ አካላት እየታየ ያለ እንደዚህ አይነት ግፍ መነሻው የትህዴን ታጋዮች ወደ ከተማዋ ገብተው እየወጡ ነው ከሚል ስጋት የመነጨ መሆኑን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።