Saturday, August 22, 2015

በአብደ ራፊዕ እና አካባቢው ሃብታቸውን እንዲያሰማሩ በስርአቱ የተጠሩት የትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች መሬታቸውን እየተነጠቁ ከቦታው እየተባረሩ መሆናቸውን ታወቀ።



    በአማራ ክልል፤ አብደ ራፊዕና አካባቢ ባለው ሰፊ የእርሻ ቦታ  እንዲሰማሩ በስርዓቱ ጥሪ የተደረገላቸው ኢትዮጵያውያን የትግራይ ተወላጆች ያላቸውን ሃብት አፍስሰው ይሰሩበት ከነበረው የእርሻ ስራ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች በዚህ ቦታ ላይ የሚመለከታችሁ መሬት የለም ወደ አገራችሁ ሂዱ በማለት መሬታቸውን ነጥቀው እያባረሯቸው እንደሆኑ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።
    መረጃው በማከል ባለሃብቶቹ በህጋዊ መንገድ ተስጥቷቸው ለዓመታት ሰርተው በሰበሰቡት ገንዘብ ወጪ አድርገው ያለሙትና ያዘጋጁት መሬት ተነጥቀው ከተባረሩ በኋላ የነበራቸውን ትራክተርና ሌሎች ንብረቶቻቸው ይዘው ወደ ሑመራ ከተማ በመሄድ ለዞንና ለወረዳ አስተዳዳሪዎች አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ እንዳላገኙና ከተበዳዮቹ ውስጥም አቶ ሽሻይ የተባሉ የሚገኙባቸው በሁመራ ከተማ ያለ ስራ ቁጭ ብለው እየዋሉ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።