Tuesday, December 29, 2015

በዚህ አመት በእቅድ የተያዙ የኤልትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በፋይናንሳዊ አቅርቦት እጥረት ምክንያት ስራቸዉ መጀመር እንዳልቻሉ ታዉቀዋል።



   በኢህኣዴግ የይስሙላ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአከባቢና ተፈጥሮ ሃፍት ጉዳይ ቀዋሚ ኮሚቴ በሚንስተር ፅፈት ቤት የወሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ተጠሪ የ2008 ዓ.ም የመጀመርያ ሩብ አመት አስመልክቶ በታሕሳስ 4/ 2008 ዓ.ም በገመገመበት ግዜ እንደተገለፀው።
    በሚቀትለው ሁለተኛ የትራንስፎርሞሽን እቅድ የተያዙ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለመስራት የሚዉል የተሰላ ባጀት ባለመኖሩ እስከአሁን ድረስ የተጀመረ ስራ እንደሌለ እና ለቀጣይም የባጀት እጥረት ስላለ በመግስት አቅም ሊሰሩ እንደማይችሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሓላፊ ኢንጂነር አዜብ ኣስናቀ መግለፃቸውን ታዉቀዋል።
     ባለ ስልጣኑ የሰጡት ሰፊ ማብራራያ እንደሚያመለክተው። በዚህ አመት ወደ ተግባር በመግባት እንዲሰሩ በእቅድ ከተያዙ የኤልክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ጭሞጋ ይዳ 278 ሚጋ ዋት፤ ገባ 214 ሜጋ ዋት፤ ሐለሌ ወራቤሳ 422 ሜጋ ዋት፤ ኣይሳ የንፋስ ሃይል ማመንጫ 300 ሜጋ ዋት የማመንጨት ኣቅም ኣላቸው የተባሉ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ፣ እስካሁን የመገንባት ሂደታቸው እናዳልጀመሩ የደረሰን መረጃ ኣመለከተ።